HadeethEnc · 1.23.0
እነዚህ ሁለቱ ከኡመቴ በወንዶቹ ላይ ክልክል ናቸው። ለሴቶቹ ግን የተፈቀደ ነው።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከዐሊይ ቢን አቢጧሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሐር በግራ እጃቸው ወርቅ በቀኝ እጃቸው በመያዝ ከዚያም እነሱን በእጃቸው ከፍ አደረጉና እንዲህ አሉ: "እነዚህ ሁለቱ ከኡመቴ በወንዶቹ ላይ ክልክል ናቸው። ለሴቶቹ ግን የተፈቀደ ነው።"»
02
Explanation
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሐር ልብስ ወይም ቁራጩን በግራ እጃቸው ይዘው የወርቅ ጌጥ ወይም መሰል ነገር ደሞ በቀኝ እጃቸው ያዙና እንዲህ አሉ: ለወንዶች ሐርና ወርቅ መልበሳቸው ክልክል ነው። ለሴቶች ግን የተፈቀደ ነው።
03
Benefits
ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: «(ክልክል) ያሉት በመልበስ መጠቀሙን ነው። ያለበለዚያማ በመመንዘር፣ በመመፅወት፣ በንግድ መጠቀሙ ለሁሉም ፆታ የተፈቀደ ነው። ወርቅን በእቃ መልክ ማድረግና በእቃ መልክ አድርጎ መጠቀሙ ደግሞ ለሁሉም ፆታ ክልክል ነው።»
የእስልምና ሸሪዓ ሴቶች ማጌጥና የመሳሰሉትን ከመፈለጋቸው አንፃር ህጉን ለነሱ ሰፋ እንዳደረገላቸው እንረዳለን።
የእስልምና ሸሪዓ ሴቶች ማጌጥና የመሳሰሉትን ከመፈለጋቸው አንፃር ህጉን ለነሱ ሰፋ እንዳደረገላቸው እንረዳለን።
Attribution
[رواه أبو داود والنسائي وابن ماجه]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

