አንዳችሁ የሞተ ጊዜ ለርሱ ጧትም ማታም ማረፊያው ይቀርብለታል።
ከዐብደላህ ቢን ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: «አንዳችሁ የሞተ ጊዜ ለርሱ ጧትም ማታም ማረፊያው ይቀርብለታል። የጀነት ነዋሪ ከሆነ የጀነት ነዋሪዎች (ማረፊያ) የእሳት ነዋሪ ከሆነም የእሳት ነዋሪዎች (ማረፊያ እየቀረበለት) "አላህ የትንሳኤ ቀን እስኪቀሰቅስህ ድረስ…

