‹ከፈለግሽ ታግሰሽ ላንቺ ጀነት አለሽ። ከፈለግሽ ደሞ ጤናን እንዲለግስሽ አላህን እለምንልሻለሁኝ።›
ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ኢብኑ ዓባስ ለዐጧእ ቢን አቢ ረባሕ እንዲህ አሉ:«ከጀነት ሰዎች መካከል የሆነች ሴት አላሳይህምን?" እኔም "እንዴታ!" አልኩኝ። እርሳቸውም እንዲህ አሉኝ: "ይህቺ ጥቁር ሴት ናት። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ መጣችና እንዲህ አለች: ‹እኔ የሚጥል በሽታ አለብኝና እገላለጣለሁ። እንዲፈውሰኝ አላህን ለምኑልኝ።› እርሳቸውም…

