ወደ ቅናቻ የተጣራ ሰው የተከተሉትን ሰዎች አምሳያ ምንዳ ያገኛል። ይህም (ለርሱ የሚሰጠው ምንዳ) ከምንዳቸው አንዳች ሳይቀነስ ነው።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "ወደ ቅናቻ የተጣራ ሰው የተከተሉትን ሰዎች አምሳያ ምንዳ ያገኛል። ይህም (ለርሱ የሚሰጠው ምንዳ) ከምንዳቸው አንዳች ሳይቀነስ ነው። ወደ ጥመት የተጣራ ሰውም የተከተሉትን ሰዎች አምሳያ ወንጀል ይኖርበታል። ይህም (በርሱ ላይ የሚኖረው ወንጀል) ከወ…

