HadeethEnc · 1.23.0
‹በዚህ በመመሪያችን ውስጥ ከርሱ (ከትእዛዛችን) የሌለን አዲስ ነገር የፈጠረ ሰው እርሱ (የፈጠረው አዲስ ነገር) ተመላሽ ነው።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከእናታችን ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: ‹በዚህ በመመሪያችን ውስጥ ከርሱ (ከትእዛዛችን) የሌለን አዲስ ነገር የፈጠረ ሰው እርሱ (የፈጠረው አዲስ ነገር) ተመላሽ ነው።›" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። በሙስሊም ዘገባ "ትእዛዛችን የሌለበትን ስራ የሰራ ሰው እርሱ (ሥራው) ተመላሽ ነው።"
02
Explanation
በሃይማኖት ውስጥ አዲስ ነገር የፈጠረ ወይም ቁርአናዊና ሐዲሣዊ ማስረጃ ያልጠቆሙትን ስራ የሰራ ሰው በባለቤቱ ላይ ተመላሽ እንደሚሆንና አላህ ዘንድም ተቀባይነት እንደማይኖረው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገለፁ።
03
Benefits
አምልኮ የተመሰረተው በቁርአንና ሐዲሥ ላይ በመጣው ላይ ስለሆነ አላህን የምናመልከው በደነገገው ድንጋጌ መሰረት እንጂ በተፈጠሩና በተፈበረኩ አምልኮዎች አይደለም።
የኢስላም ሃይማኖት ተግባራዊነት በግላዊ ምልከታና አንድን ነገር መልካም አድርጎ በማየት ሳይሆን መልክተኛውን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመከተል ነው።
ይህ ሐዲሥ የኢስላምን ምሉእነት የሚጠቁም ነው።
ቢድዓ (መጤ) ማለት: በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘመንና በሶሐቦች ዘመን ያልነበረ ሁሉም በሃይማኖት ውስጥ የተፈጠረ እምነታዊ ጉዳይ ወይም ንግግር ወይም ተግባር ነው።
ይህ ሐዲሥ ከኢስላም መሰረቶች መካከል አንድ መሰረት የሆነና ለተግባራቱም እንደሚዛን የሆነ ሐዲሥ ነው። የትኛውም የአላህ ፊት ያልተፈለገበት ስራ ባለቤቱ በስራው ምንዳ እንደማያገኝበት ሁሉ ልክ እንደዚሁ መልክተኛው (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይዘው የመጡትን ያልገጠመ የትኛውም ስራም በባለቤቱ ላይ ተመላሽ ይሆናል።
የተከለከለው አዲስ ፈጠራ ሃይማኖታዊ ጉዳይ ላይ ነው እንጂ አለማዊ ጉዳይ ላይ አይደለም።

Attribution
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares