አንድ ሰውዬ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) 'ማንኛው የኢስላም ክፍል ነው ምርጡ?' ብሎ ጠየቀ። እርሳቸውም 'ምግብ መመገብህ፣ ሰላምታን ባወቅከውም ባላወቅከውም ሰው ላይ ማቅረብህ ነው።' ብለው መለሱለት።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:- "አንድ ሰውዬ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) 'ማንኛው የኢስላም ክፍል ነው ምርጡ?' ብሎ ጠየቀ። እርሳቸውም 'ምግብ መመገብህ፣ ሰላምታን ባወቅከውም ባላወቅከውም ሰው ላይ ማቅረብህ ነው።' ብለው መለሱለት።"
Explanation
የመጀመሪያው: ድሃዎችን ማብላትን ማብዛት ነው። እዚህ ውስጥም ሶደቃ፣ ስጦታ፣ ግብዣ፣ የሰርግ ድግስ ይገባሉ። የማብላቱ በላጭነትም በረሃብና ኑሮ በተወደደበት ወቅት የጠነከረ ይሆናል።
ሁለተኛው: አወቅከውም አላወቅከውም በሁሉም ሙስሊም ላይ ሰላምታን ማቅረብ ነው።
Benefits
ሰላምታ ማቅረብና ምግብ ማብላት ሰዎች በሁሉም ወቅት የሚፈልጉት ስለሆነና በላጭ ስራ ከመሆኑ አንፃር በኢስላም ውስጥ ትልቅ ደረጃ ከሚሰጣቸው ተግባራት መካከል እንደሆኑ እንረዳለን።
በነዚህ ሁለት ጉዳዮች ንግግራዊም ተግባራዊም በጎነት ይሰበሰባሉ። ይህም የተሟላው በጎነት ነው።
እነዚህ ጉዳዮች ሙስሊሞች በመካከላቸው ሊኖራቸው ከሚገባው መስተጋብር ጋር የተያያዘ ሲሆን ሌላ ቦታ ደግሞ አንድ ባሪያ ከጌታው ጋር ሊኖረው ስለሚገባ መስተጋብር የሚገልፁ ጉዳዮች አሉ።
በሰላምታ መጀመር በሙስሊሞች መካከል ብቻ የተገደበ ሲሆን ካፊር በሰላምታ አይጀመርም።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

