ለአንድ ሰው ወንድሙን ከሶስት ሌሊቶች በላይ ሊያኮርፈው አይፈቀድለትም። ሲገናኙ ይህም ይዞራል ያኛውም ይዞራል። ከሁለቱ ምርጡ ሰላምታ የሚጀምረው ነው።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአቡ አዩብ አልአንሷሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "ለአንድ ሰው ወንድሙን ከሶስት ሌሊቶች በላይ ሊያኮርፈው አይፈቀድለትም። ሲገናኙ ይህም ይዞራል ያኛውም ይዞራል። ከሁለቱ ምርጡ ሰላምታ የሚጀምረው ነው።"
Explanation
ከነዚህ ሁለት ጠበኞች መካከል በላጩ ኩርፊያውን ለማስወገድ የሚሞክርና ሰላምታ የሚጀምረው ነው። እዚህ ሐዲስ ውስጥ ኩርፊያ በማለት የተፈለገው በነፍሱ ፍላጎቶች ያኮረፈ ከሆነ ነው። ወንጀለኞችን፣ የቢድዓ ባለቤቶችንና መጥፎ ጓደኞችን የመሰሉ ሰዎችን ለአላህ ሀቅ ብሎ ማኩረፍ ከሆነ ግን በወቅት ሳይሆን የሚገደበው ኩርፊያው በሚያመጣው ጥቅምና ያለባቸው ችግር በመወገዱ ላይ ነው የሚገደበው።
Benefits
ሰላምታ ነፍሶች ውስጥ ያለን አለመግባባት ማስወገዱና የመዋደድ ምልክትም በመሆኑ የሰላምታን ደረጃ ያስረዳናል።
ኢስላም በወንድማማችነት ላይና በአማኞቹ አንድነት ዙሪያ መጓጓቱን እንረዳለን።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

