HadeethEnc · 1.23.0
በደልን ተጠንቀቁ! በደል የትንሳኤ ቀን ድርብርብ ጨለማዎች ነውና። ስስትንም ተጠንቀቁ! ስስት ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች አጥፍቷልና።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከጃቢር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በደልን ተጠንቀቁ! በደል የትንሳኤ ቀን ድርብርብ ጨለማዎች ነውና። ስስትንም ተጠንቀቁ! ስስት ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች አጥፍቷልና። ስስታምነት ደማቸውን እንዲያፈሱና ሐራም (ያልተፈቀደውን) እንደ ሐላል አድርገው እንዲቆጥሩ አነሳስቷቸዋልና።"
02
Explanation
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከበደል አስጠነቀቁ። ከበደል መካከልም: ሰዎችን መበደል፣ ነፍስን መበደል፣ በአላህ ሐቅ ላይ በደል መፈፀም ይጠቀሳሉ። በደል ማለት ሁሉንም የሐቅ ባለቤቶችን ሐቃቸውን ከመስጠት መተው ነው። በደል የትንሳኤ ቀን በባለቤቱ ላይ ከሚያጋጥመው መከራዎችና አስፈሪ ክስተቶች አኳያ ጨለማ ነው። ከስስትም ከለከሉ። እርሱም ከመጓጓት (መንሰፍሰፍ) ጋር እጅግ ስስታምነት ነው። ከስስታምነት መካከል: ገንዘባዊ ሐቆችን ከመወጣት ቸል ማለትና ለዱንያ እጅግ መንገብገብም ይጠቀሳል። ይህኛው የበደል ክፍል ማለትም ስስታምነት ከእኛ በፊት የነበሩትን ህዝቦች አጥፍቷቸዋል። ይህም ከፊሉ ከፊሉን እንዲገድሉና አላህ እርም ያደረጋቸውን ክልክሎች የተፈቀዱ እንዲያደርጉ አነሳስቷቸዋል።
03
Benefits
ገንዘብን ማውጣትና ወንድማዊ መረዳዳት ከመዋደድና ከመቀራረብ ሰበቦች መካከል አንዱ ነው።
ስስታምነትና ስግብግብነት ወደ ወንጀል፣ ኃጢአትና ብልግና ይጎትታል።
ካለፉት ህዝቦች ሁኔታ ትምህርት መውሰድ እንደሚገባ እንረዳለን።
ስስታምነትና ስግብግብነት ወደ ወንጀል፣ ኃጢአትና ብልግና ይጎትታል።
ካለፉት ህዝቦች ሁኔታ ትምህርት መውሰድ እንደሚገባ እንረዳለን።
Attribution
[ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

