
መጾም
لوحة الصيام (ፊቅሁ አስሲያም) የፆም ህግጋት በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ በራሪ ወረቀት፣ የተዘጋጀው በዶክተር ሀይሰም ሰርሀን ሲሆን በውስጡ ከግዴታና ሱና (የተወደዱ)ፆሞች ጋር የተያያዙ ነጥቦች፣ ፆም መፆም የተጠላበትና የተከለከለበትን ወቅቶችን አውስቷል። اللغة أمهرية በአማርኛ ቋንቋ ፆም ሁለት አይነት ነው الصيام...
መጾም
لوحة الصيام
(ፊቅሁ አስሲያም) የፆም ህግጋት
በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ በራሪ ወረቀት፣
የተዘጋጀው በዶክተር ሀይሰም ሰርሀን ሲሆን በውስጡ ከግዴታና ሱና (የተወደዱ)ፆሞች ጋር የተያያዙ ነጥቦች፣ ፆም መፆም የተጠላበትና የተከለከለበትን ወቅቶችን አውስቷል።
اللغة أمهرية
በአማርኛ ቋንቋ
ፆም ሁለት አይነት ነው
الصيام قسمان
ዋጂብ የሆኑ፡ የረመዷን ፆም፣ የከፋራህ ፆም እና የስለት ፆም ናቸው
واجب : في رمضان و الكفارات و النذور
ነፍል(ሱና የሆኑ)፡ ከነዚህ ውጭ ያሉት ናቸው
نفل : في غير ذلك
የ ፆም ማብራሪያ፡
تعريف الصيام
ፆም ብሎ ማለት ትክክለኛው ፈጅር ከወጣበት ሰአት ጀምሮ ፀሃይ እስከምትጠልቅበት ሰአት ድረስ ከምግብ ፣ ከመጠጥ እንዲሁም ከማንኛውም የሚያስፈጥሩ ነገራቶች እራሳችንን በመቆጠብ አላህን የምንገዛበት የ ዒባዳ አይነት ነው።
هو التعبّد لله عز وجل بالإمساك عن الطعام والشراب وسائر المفطّرات منطلوع الفجر الصادق إلى غروب الشمس.
ለፆም ሁለት ማእዘናቶች አሉት
للصيام ركنان
1 - ኒያህ
1 - الــنــيّة
የግዴታ ፆም ኒያህ፡
نيّة الفرض :
ለግዴታ ፆም ኒያውን ማሳደር አለበት(ማለትም ከፈጂር በፊት ቀኑን በፆም እንደሚያሳልፍ መወሰን መነየት አለበት)
ለእያንዳንዱ ቀን ራሱን የቻለ ኒያህ ያስፈልገዋል። የኒያ ቦታዋ ደግሞ ቀልብ ነው። በምላስ ድምፅን አውጥቶ ማለት ቢድዓ ነው።
لابدّ من تبييت النيّة في الفرض من الليل - أي:قبل الفجر - , ويكفي عقد النيّة بدخول الشهرفي رمضان , ومحلها القلب , والتلفظ بها بدعة.
የነዋፊል(የሱና) ፆም ኒያህ፡
نيّة النفل :
የሚያስፈጥር ነገር እስካልፈፀመ ድረስ በማንኛውም የቀኑ ክፍል መነየት ይችላል። ነገር ግን አጅሩ የሚታሰብለት ኒያ ካደረገበት ሰአት ጀምሮ ነው።
تصحّ في أي ساعة من النهارما لم يأت بمفطّر , ولكن يحسب الأجر من عقد النية.
2 - ከሚያስፈጥሩ ነገራቶች መታቀብ
2- الإمساك عن المفطرات
ፆምን የሚያበላሹ ነገራቶች፡
مفسدات الصيام :
1 አውቆ መብላትና መጠጣት፣ ረስቶ ከሆነ ግን ፆሙ አይበላሽም።
-1 الأكل أو الشرب عمداَ , فمن نسي فصيامه صحيح
2 ፆታዊ ግኙነት ማድረግ፣ይህንን የፈፀመው በረመዷን ቀን ላይ ከሆነ ከባድ የሆነ ከፋራ(ማሳበሻ) ያስፈልገዋል
-2 الجماع , فإذا كان في نهار رمضان والصوم واجب عليه لزمته الكفارة المغلظة
3 መንይን ማፍሰስ
-3 إنزال المني
4 ምግብን የሚተኩ ነገራቶችን መጠቀም ለምሳሌ የምግብ መርፌ(ግሉኮዝ)
-4 ما كان بمعنى الأكل والشرب , مثل الإبر المغذية
5 በዋግምት ደምን ማውጣት
-5 إخراج الدم بالحجامة
6 አውቆ ማስታወክ
-6 التقيؤ عمداّ
7 የወሊድ ደም እና የወር አበባ ደም መፍሰስ
-7 خروج دم الحيض و النفاس
ለፆመኛ ከሚፈቀዱ ነገራቶች
بعض ما يباح للصائم
• ለሓጃ ምግብ መቅመስ
• ምራቅን መዋጥ
• ሻወር መውሰድ
• ሲዋክ መጠቀም
• ሽቶ መቀባት
• ራስን ማቀዝቀዝ
- ذوق الطعام لحاجة
- بلع الريق
- الاغتسال
- السواك
- التطيب
- التبرّد
የፆም መስፈርቶች
شروط وجوب الصيام
1 ኢስላም
1 - الإسـلام
2 አእምሮ ጤነኛ መሆን
2 - الـعـقل
3 ለአቅመ አዳም መድረስ፣ ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ህፃናቶች እንዲፆሙ ሊበረታቱ ይገባል።
3 - البلوغ , أما غير البالغ فيرغب في الصيام , ويأمره وليه .
4 ቋሚ ኗሪ መሆን፣ ለመንገደኛ ፆም መፆም ግድ አይሆንበትም፣ ፆሙ የማይጎዳው ከሆነ ግን በጉዞ ላይ መፆሙ የተሻለ ነው።
4 - الاستيطان: فلا يجب الصيام على المسافر , والأولى أن يصوم مالم يشقّ عليه, لفعل النبي ﷺ ولأنه أسرع في إبراء الذمة وأيسر على المكلف ولإدراك فضيلة الشهر.
5 ጤነኛ መሆን
5 - الـصّـحـة
6 ከወር አበባና ከወሊድ ደም ንፁህ መሆን
6 - الخلو من الحيض والنفاس
ለፆመኛ የሚጠሉ ነገሮች
مكروهات الصيام :
1 ድንበር ያለፈ ባፍንጫ ውሃ መሳብና መጉመጥመጥ
-1 المبالغة في المضمضة والاستنشاق
2 ያለምንም ሓጃ ምግብን መቅመስ
-2 ذوق الطعام لغير حاجة
በፆመኛ ላይ ሓራም የሆኑ ነገራቶች
يحرم على الصائم :
1 አክታን መዋጥ
-1 بلع النخامة ولا يفطر بها
2 ባለቤቱን መሳም፡ ፆሙን እንደማይፈታ እርግጠኛ ላልሆነ ሰው
-2 القبلة لمن لا يأمن فساد صومه
3 ቀውለዙር (ሃራም የሆኑ ነገራቶችን መፈፀም)
-3 قول الزور (وهو فعل كل محرم)
4 ጀህል(ቂላቂልነት)
-4 الجهل ( وهو السفاهة)
5 ፆምን ሳያፈጥሩ ለተከታታይ ቀናት መፆም
-5 الوصال ( أي ألا يفطر يومينمتتاليين)
6 በዋግምት ደምን ማስወጣት
-6 إخراج الدم بالحجامة
7 አውቆ ማስታወክ
-7 التقيؤ عمداّ

መጾም
Scan QR Code | Use a QR Code Scanner to fast download directly to your mobile device