Prophetic Hadeeth Encyclopedia
Search and read verified Prophetic hadeeth translations, explanations, benefits, categories and source attribution. Page 6.
Search the Hadeeth Encyclopedia
Smart instant results tolerate minor spelling mistakes, with every filter in one place.
በአላህ ማመን
እኔ የበኑ ሰዕድ ቢን በክር ወንድም ዲማም ቢን ሠዕለባህ ነኝ።" አላቸው።
አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ መስጂድ ውስጥ ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ጋር ተቀምጠን ሳለ አንድ ግመል ላይ ያለ ሰውዬ ገባ። መስጂድ ውስጥ ግመሉን ካንበረከከ በኋላ አሰራት። ከዚያም ለነሱ እንዲህ አላቸው፦ "ማንኛችሁ ነው ሙሐመድ?" ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በመካከላቸው ተደግፈው ነበር። "ይህ የተደገፈው ቀይ ሰውዬ ነው።" አልነው…
ያ በዱንያ ውስጥ እያሉ በሁለት እግራቸው እንዲሄዱ ያደረጋቸው የትንሳኤ ቀን በፊታቸው እንዲሄዱ ማድረግ የሚችል አይደለምን?
ቀታዳህ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦ አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደነገሩን አንድ ሰው "የአላህ ነቢይ ሆይ! ከሓዲዎች በትንሣኤ ቀን እንዴት በፊቶቻቸው እየተሳቡ ይቀሰቀሳሉ?" አላቸው። እርሳቸውም " ያ በዱንያ ውስጥ እያሉ በሁለት እግራቸው እንዲሄዱ ያደረጋቸው የትንሳኤ ቀን በፊታቸው እንዲሄዱ ማድረግ የሚችል አይደለምን?" አሉት። ቀታዳህ እንዲህ አሉ፦ "በጌታዬ ልቅና ይሁንብኝ እንዴ…
አላህ ለናንተ ሶስት ነገር ይወድላችኋል፤ ሶስት ነገርንም ይጠላባችኋል።
ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ ለናንተ ሶስት ነገር ይወድላችኋል፤ ሶስት ነገርንም ይጠላባችኋል። እርሱን መገዛታችሁን፣ በርሱ ላይ አንዳችንም አለማጋራታችሁን፣ ሁላችሁም በአላህ ገመድ መተሳሰራችሁንና አለመለያየታችሁን ለናንተ ይወድላችኋል።…
እስልምና በአምስት መሰረቶች ተገነባ
ከአቡ ዐብዱረሕማን ዓብደላህ ቢን ዑመር ቢን ኸጧብ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: «እስልምና በአምስት መሰረቶች ተገነባ እነርሱም: 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወአንነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ' (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ሙሐመድም የአላህ ባሪያና መልክተኛ ናቸው።) ብሎ መመስከር፣…
እናንተ ሰዎች ሆይ! አላህ መልካም ነው። ከመልካም በቀርም አይቀበልም። አላህ መልክተኞችን ባዘዘው ነገር አማኞችንም አዟል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "አላህ መልካም (ጥሩ) ነውና ከመልካም (ከጥሩ) በቀር አይቀበልም። አላህ መልክተኞችን ባዘዘበት ነገር አማኞችንም አዟል። አላህ እንዲህ ብሏል: {እናንተ መልክተኞች ሆይ! ከተፈቀዱት ምግቦች ብሉ። በጎ ስራንም ስ…
አንተ ልጅ ሆይ! እኔ ቃላቶችን አስተምርሃለሁ! የአላህን (ትእዛዛት) ጠብቅ (አላህ) ይጠብቅሀል፤ የአላህን (ትእዛዛት) ጠብቅ ፊት ለፊትህ ታገኘዋለህ፤ የጠየቅክ ጊዜ አላህን ጠይቅ! ፤ እገዛን የፈለግክ ጊዜም በአላህ ታገዝ!
ከአቡል ዐባስ ዐብደላህ ቢን ዓባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «አንድ ቀን ከአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ኋላ ነበርኩ። እንዲህም አሉኝ: "አንተ ልጅ ሆይ! እኔ ቃላቶችን አስተምርሃለሁ! የአላህን (ትእዛዛት) ጠብቅ (አላህ) ይጠብቅሀል፤ የአላህን (ትእዛዛት) ጠብቅ ፊት ለፊትህ ታገኘዋለህ፤ የጠየቅክ ጊዜ አላህን ጠይቅ! ፤ እገዛን የፈለግክ ጊዜ…
በኢስላም ውስጥ ከርሶ ውጪ ስለርሱ አንድንም ሰው የማልጠይቀው የሆነን አንድን ንግግር ንገሩኝ አልኳቸው። እርሳቸውም 'በአላህ አምኛለሁ በል ከዚያም ቀጥ በል።' አሉኝ
አላህ መልካሞችና ኃጢዐቶችን ፅፏል። ይህንንም አብራርቶታል።
ከኢብኑ ዓባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከተከበረውና ከላቀው ጌታቸው በሚያስተላልፉት (ሐዲሠል ቁድሲይ) እንዲህ አሉ፦ "አላህ መልካሞችና ኃጢዐቶችን ፅፏል። ይህንንም አብራርቶታል። አንድን መልካም ስራ (ለመስራት) አስቦ ያልሰራት አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ሙሉ ምንዳን ይጽፍለታል። እሱ (ለመስራት) አስቦ ከሰራት ደግሞ አላህ እሱ…
አላህ እንዲህ ብሏል: ‹የኔን ወዳጅ (ወሊይ) ጠላት አድርጎ የያዘን ሰው በርግጥም ጦርነት እንዳወጀኩበት አሳውቄዋለሁ። ባሪያዬ ግዴታ ካደረግኩበት በበለጠ ወደ እኔ ተወዳጅ በሆነ በአንዳችም ነገር አይቃረብም።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ እንዲህ ብሏል: ‹የኔን ወዳጅ (ወሊይ) ጠላት አድርጎ የያዘን ሰው በርግጥም ጦርነት እንዳወጀኩበት አሳውቄዋለሁ። ባሪያዬ ግዴታ ካደረግኩበት በበለጠ ወደ እኔ ተወዳጅ በሆነ በአንዳችም ነገር አይቃረብም። ባሪያዬ ወደ እኔ በትርፍ ስራዎች ከመቃረብ አ…

