እርሱ ውሃው አፅጂ ነው፤ ውስጡ የሞተም ሐላል ነው።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «አንድ ሰው የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ በማለት ጠየቀ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኛ በባህር እንሳፈራለን፣ ከኛ ጋርም የተወሰነ ውሃ እንሰንቃለን። በዚህ በያዝነው ውሃ ዉዱእ ብናደርግበት እንጠማለንና በባህር ውሃ ዉዱእ እናድርግን?" የአላህ መልክተኛም…

