HadeethEnc · 1.23.0
እርሱ ውሃው አፅጂ ነው፤ ውስጡ የሞተም ሐላል ነው።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «አንድ ሰው የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ በማለት ጠየቀ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኛ በባህር እንሳፈራለን፣ ከኛ ጋርም የተወሰነ ውሃ እንሰንቃለን። በዚህ በያዝነው ውሃ ዉዱእ ብናደርግበት እንጠማለንና በባህር ውሃ ዉዱእ እናድርግን?" የአላህ መልክተኛም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ በማለት መለሱ: "እርሱ ውሃው አፅጂ ነው፤ ውስጡ የሞተም ሐላል ነው።"»
02
Explanation
አንድ ሰውዬ ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ በማለት ጠየቀ "እኛ ለማደን ወይም ለንግድና ለመሳሰሉት በባህር ላይ ጀልባዎችን እንሳፈራለን። ለመጠጥ የሚሆን ትንሽ ውሃንም ከኛ ጋር እንጭናለን። የመጠጡን ውሃ ለዉዱእና ለገላ ትጥበት ከተገለገልን ያልቅብንና የምንጠጣውን አናገኝም። ታዲያ በባህር ውሃ ዉዱእ ማድረግ ለኛ ይፈቀድልናል እንዴ?"
ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ስለባህሩ ውሃ እንዲህ አሉ "ውሃው ንፁህም አፅጂም ነው። በርሱም ዉዱእ ማድረግ፣ ገላ መታጠብ ይፈቀዳል። ከርሱ የሚወጡን አሳዎችንና ሌሎች የባህር እንስሳዎችንም ሙተው ሳይታደኑ ከላይ ተንጣለው ቢገኙ ራሱ መብላት ይፈቀዳል።"
ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ስለባህሩ ውሃ እንዲህ አሉ "ውሃው ንፁህም አፅጂም ነው። በርሱም ዉዱእ ማድረግ፣ ገላ መታጠብ ይፈቀዳል። ከርሱ የሚወጡን አሳዎችንና ሌሎች የባህር እንስሳዎችንም ሙተው ሳይታደኑ ከላይ ተንጣለው ቢገኙ ራሱ መብላት ይፈቀዳል።"
03
Benefits
የባህር እንስሳ ቢሞት ሐላል ነው። ውስጡ የሞተ በማለት የሚፈለገው: በባህር ውስጥ ካልሆነ በቀር የማይኖር ሆኖ እዛው ውስጥ የሞተን ነው።
የተሟላ ጥቅም እንዲገኝ ጠያቂ ከጠየቀው በበለጠ መመለስ እንደሚገባ እንረዳለን።
ውሃ ውስጡ በገባበት ንፁህ ነገር ጣዕሙ ወይም ቀለሙ ወይም ሽታው ቢለወጥ ውሃው በተፈጥሮ ባህሪው ላይ እስከቀረ ድረስ ጨዋማነቱ ወይም ትኩስነቱ ወይም ቀዝቃዛነቱና የመሳሰሉ ነገሮች ቢበረቱ ራሱ አፅጂ እንደሆነ ይቀራል።
የባህር ውሃ ትንሹንም ሆነ ትልቁን ሐደሥ ያነሳል። ንፁህ በሆነ ሰውነት ወይም ልብስ ወይም ከዛ ውጪ ላይ ያረፈን ነጃሳ ራሱ ያስወግዳል።

Attribution
[رواه أبو داود والترمذي والنسائي وابن ماجه وأحمد]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares