HadeethEnc · 1.23.0
ውሃው ሁለት 'ቁለተይን' ከደረሰ ነጃሳን አይሸከምም።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከዐብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንስሶችና አውሬዎች ተመላልሰው ስለሚጠጡት ውሃ ተጠየቁ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ: "ውሃው ሁለት 'ቁለተይን' ከደረሰ ነጃሳን አይሸከምም።"»
02
Explanation
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንስሳዎችና አውሬዎች ለመጠጣትና ለመሳሰሉት ስለሚመላለሱበት ውሃ ንፁህነት ብይን ተጠየቁ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ውሃ መጠኑ ሁለት ትላልቅ እንስራዎችን የደረሰ ጊዜ ‐ 210 ሊትር የሚሆን ብዛት ማለት ነው። ‐ ብዙ ውሃ ስለሆነ ከሶስቱ ባህሪያቶቹ አንዱ በነጃሳ እስካልተለወጠ ድረስ እነርሱም ቀለሙ ወይም ጣዕሙ ወይም ሽታው እስካልተለወጠ ድረስ አይነጀስም አሉ።
03
Benefits
ውሃ ከሶስቱ ባህሪያቶቹ አንዱ በነጃሳ የተለወጠ ጊዜ ማለትም ቀለሙ ወይም ጣዕሙ ወይም ሽታው የተለወጠ ጊዜ ይነጀሳል። ሐዲሡ በአብዛኛው ጊዜ ከሚከሰተው በመንተራስ ነው የተነገረው እንጂ በመገደብ ደረጃ አይደለም።
ውሃ በነጃሳ የተለወጠ ጊዜ ውሃው አነሰም በዛ እንደሚነጀስ ዑለማዎች ባጠቃላይ ተስማምተዋል።
ውሃ በነጃሳ የተለወጠ ጊዜ ውሃው አነሰም በዛ እንደሚነጀስ ዑለማዎች ባጠቃላይ ተስማምተዋል።
Attribution
[رواه أبو داود والترمذي والنسائي وابن ماجه وأحمد]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

