ከአንተ በፊት ማንም ያልተሰጠው በሆነ ለአንተ ብቻ በተሰጠህ ሁለት ብርሃኖች አበስርሃለሁ። (እነርሱም) የመጽሐፉ መክፈቻ (ፋቲሓ) እና የበቀራ ምዕራፍ መጨረሻዎቹ ናቸው። ከነርሱም አንድም ፊደል አታነብም የሚሰጥህ ቢሆን እንጂ።
ከኢብኑ ዐባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ጂብሪል ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ ተቀምጦ ሳለ ከበላዩ ድምፅ ሰማና ራሱን ቀና አደረገ። እንዲህም አለ: "ይህ ዛሬ የተከፈተ የሰማይ በር ነው። ከዛሬ በቀርም ተከፍቶ አያውቅም።" ከተከፈተው በርም መልአክ ወረደ። ጂብሪልም እንዲህ አለ: "ይህ ወደ ምድር የወረደ መልአክ ነው። ከዛሬ…

