HadeethEnc · 1.23.0
ለቁርኣን ባለቤት "አንብብ! (ደረጃን) ውጣ! በዱንያ ውስጥ አሳምረህ ታነብ እንደነበርከው አሳምረህ አንብብ! (ጀነት ውስጥ) ያንተ ስፍራ የምታነበው የመጨረሻው አንቀፅ ዘንድ ነው።" ይባላል።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ዐብደላህ ቢን ዐምር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "ለቁርኣን ባለቤት "አንብብ! (ደረጃን) ውጣ! በዱንያ ውስጥ አሳምረህ ታነብ እንደነበርከው አሳምረህ አንብብ! (ጀነት ውስጥ) ያንተ ስፍራ የምታነበው የመጨረሻው አንቀፅ ዘንድ ነው።" ይባላል።"
02
Explanation
ቁርኣንን ለሚያነብ፣ ቁርኣን ውስጥ ባለው ለሚሰራ፣ በቃሉ መሸምደድንም ሆነ አሳምሮ ማንበብን አጥብቆ የያዘ ጀነት በሚገባ ጊዜ "ቁርኣንን አንብብ! በዚህም ሰበብ የጀነት ደረጃዎችን ውጣ! ቁርኣንን በስክነትና እርጋታ ዱንያ ላይ ታነበው እንደነበርከው አንብብ! ያንተ ስፍራ የምታነበው የመጨረሻው አንቀፅ ዘንድ ነው።" ይባላል በማለት ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ተናገሩ።
03
Benefits
በቁጥርም ሆነ በሁኔታ ለሥራችን በሚመጥን መልኩ ነው የምንመነዳው።
ቁርኣንን በማንበብ፣ አሳምሮ በመቅራት፣ በመሸምደዱ፣ በማስተንተኑና በቁርኣን በመስራት ላይ መበረታታቱን እንረዳለን።
ጀነት በርካታ ደረጃዎችና እርከኖች ያሏት ሲሆን የቁርኣን ባለቤት የሆነ ሰው ከፍተኛ የሆነውን ደረጃ ነው የሚያገኘው።
ቁርኣንን በማንበብ፣ አሳምሮ በመቅራት፣ በመሸምደዱ፣ በማስተንተኑና በቁርኣን በመስራት ላይ መበረታታቱን እንረዳለን።
ጀነት በርካታ ደረጃዎችና እርከኖች ያሏት ሲሆን የቁርኣን ባለቤት የሆነ ሰው ከፍተኛ የሆነውን ደረጃ ነው የሚያገኘው።
Attribution
[አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ነሳኢ በኩብራ፣ አሕመድ ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

