ወንድ ልጅ ወደ ወንድ ልጅ ሀፍረተ ገላ አይመልከት! ሴት ልጅም ወደ ሴት ልጅ ሀፍረተ ገላ አትመልከት!
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ወንድ ልጅ ወደ ወንድ ልጅ ሀፍረተ ገላ አይመልከት! ሴት ልጅም ወደ ሴት ልጅ ሀፍረተ ገላ አትመልከት! ወንድ ልጅ ከሌላ ወንድ ጋር በአንድ ልብስ ውስጥ አይጠቅለል! ሴት ልጅም ከሌላ ሴት ጋር በአንድ ልብስ ውስጥ አትጠቅለል!"
Explanation
ሀፍረተ ገላ ማለት: ግልፅ የሆነ ጊዜ የሚያሳፍር የሆነ አካል ሁሉ ነው። የወንድ ልጅ ሀፍረተ ገላ ከእምብርት እስከ ጉልበቱ ሲሆን፤ የሴት ልጅ ደግሞ ከባዕድ ወንዶች አንፃር ሁሉም ሰውነቷ ሀፍረተ ገላ ነው። ከሴቶችና ከዘመዶቿ አንፃር ደግሞ በተለምዶ ቤት ውስጥ ስሰራ ግልፅ የሚሆነውን ያክል ግልፅ ታደርጋለች።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወንድ ልጅ ተራቁቶ ከሌላው ወንድ ጋር በአንድ ልብስ ውስጥ ወይም ለብቻቸው ከአንድ ብርድ ልብስ ስር መገለላቸውን ከለከሉ። ሴት ልጅም ተራቁታ ወደ ሴት ልጅ በአንድ ልብስ ውስጥ ወይም ለብቻቸው ከአንድ ብርድ ልብስ ስር መገለላቸውን ከለከሉ። ምክንያቱም ይህ አንዱ የሌላኛው ጓደኛውን ሀፍረተ ገላ ወደመንካት ያደርሰዋልና። መንካቱ ደግሞ እንደማየቱ ክልክል ነው። እንደውም ወደ ትልቅ ብክለት ስለሚያመራ መንካቱ ከማየትም በበለጠ ክልክል ነው።
Benefits
ኢስላም ማህበረሰቡን በማፅዳትና ለብልሹነት የሚያደርሱ መንገዶችን በመዝጋት ላይ ያለውን ጥረት እንረዳለን።
እንደ ህክምና ለመሰሉ ጉዳዮች ሀፍረተ ገላን መመልከት አስፈላጊ ሆኖ የተገኘ ጊዜ መመልከት ይፈቀዳል። ነገር ግን ከስሜት ውጪ በሆነ ሁኔታ መሆን ይገባዋል።
ሙስሊም ሀፍረተ ገላውን በመሸፈን ላይና የሌላን ሰው ሀፍረተ ገላ ከመመልከት አይኑን ዝቅ በማድረግ ላይ መታዘዙን እንረዳለን።
ክልከላው ወንዶችን ከወንዶች ጋር፣ ሴቶችን ከሴቶች ጋር ብቻ በመከልከል መገደቡ ማየትና ሀፍረተ ገላን መግለጥ ብዙ ጊዜ ቀለል ተደርጎ የሚታይ ስለሆነ ነው።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

