HadeethEnc · 1.23.0
የቀጭን ሐርንና የወፍራም ሐርን ልብስ አትልበሱ! በወርቅና ብር እቃ አትጠጡ! በ(ወርቅና ብር) ትሪም አትብሉ! እርሷ በዚህ ዓለም ለነርሱ ናት፤ በመጪው ዓለም ደግሞ ለኛ ናት።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከዐብዱረሕማን ቢን አቢ ለይላ እንደተላለፈው እነርሱ ሑዘይፋ ዘንድ ነበሩ። የሚጠጣ እንዲሰጡት ሲጠይቅ አንድ እሳት አምላኪ የሚጠጣ (በብር እቃ) ሰጠው። እቃውን (በሑዘይፋ) እጁ ላይ ሲያኖረውም እርሱን ወረወረበትና እንዲህ አለ: "ከአንድና ሁለት ጊዜ በላይ ባልከለክለው ኖሮ ‐ ይህን አላደርግም ነበር ‐። ነገር ግን ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "የቀጭን ሐርንና የወፍራም ሐርን ልብስ አትልበሱ! በወርቅና ብር እቃ አትጠጡ! በ(ወርቅና ብር) ትሪም አትብሉ! እርሷ በዚህ ዓለም ለነርሱ ናት፤ በመጪው ዓለም ደግሞ ለኛ ናት።"
02
Explanation
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሐርን ልብስ በየትኛውም አይነቱ ከመልበስ ወንዶችን ከለከሉ። ወንዶችንም ሴቶችንም በወርቅና ብር እቃዎችና መሳሪያ ከመብላትና ከመጠጣት ከለከሉ። ይህም አማኞች በዚህች አለም አላህን ለመታዘዝ እንደራቁት ሁሉ የትንሳኤ ቀን ደግሞ ለአማኞች ብቻ እንደሆነ ተናገሩ። ከሀዲያኖችስ በመጪው ዓለም ምንም የላቸውም። ምክንያቱም የአላህን ትእዛዝ በማመፅ ቸኩለው በዚህ ዓለም ህይወታቸው ምርጥ የሚሉትን ነገሮች በመያዝ ስለተጠቀሙ ነው።
03
Benefits
በወንዶች ላይ ቀጭንና ወፍራም ሐር ክልክል መሆኑንና የለበሰው ላይም ብርቱ ዛቻ እንዳለበት እንረዳለን።
ቀጭንና ወፍራም ሐር መልበስ ለሴቶች ይፈቀዳል።
በወንድም ሆነ በሴቶች ላይ በወርቅና ብር ትሪዎችና እቃዎች መብላትና መጠጣት ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
የሑዘይፋ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና አወጋገዝ ጠንከር ያለ መሆኑን እንመለከታለን። የዚህንም ምክንያት ከአንድ ጊዜ በላይ የወርቅና ብር እቃዎችን እንዳይጠቀም መከልከላቸውና እርሱ ግን አለመቆጠቡ እንደሆነ ገልጿል።
ቀጭንና ወፍራም ሐር መልበስ ለሴቶች ይፈቀዳል።
በወንድም ሆነ በሴቶች ላይ በወርቅና ብር ትሪዎችና እቃዎች መብላትና መጠጣት ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
የሑዘይፋ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና አወጋገዝ ጠንከር ያለ መሆኑን እንመለከታለን። የዚህንም ምክንያት ከአንድ ጊዜ በላይ የወርቅና ብር እቃዎችን እንዳይጠቀም መከልከላቸውና እርሱ ግን አለመቆጠቡ እንደሆነ ገልጿል።
Attribution
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

