HadeethEnc · 1.23.0
የሙስሊም ሽርጥ እስከ ባቱ ግማሽ ድረስ ነው። ከባቱ ግማሽና በቁርጭምጭሚቱ መሃል ቢሆንም ግን ችግር የለውም። ከቁርጭምጭሚት ዝቅ ያለ ከሆነ እርሱ እሳት ውስጥ ነው። ሽርጡን በኩራት የጎተተን ሰው አላህ ወደርሱ አይመለከትም።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦ "የሙስሊም ሽርጥ እስከ ባቱ ግማሽ ድረስ ነው። ከባቱ ግማሽና በቁርጭምጭሚቱ መሃል ቢሆንም ግን ችግር የለውም። ከቁርጭምጭሚት ዝቅ ያለ ከሆነ እርሱ እሳት ውስጥ ነው። ሽርጡን በኩራት የጎተተን ሰው አላህ ወደርሱ አይመለከትም።"
02
Explanation
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አንድ ወንድ ሙስሊም ሽርጡን ምን ማድረግ እንዳለበት ገለፁ። ሽርጥ ሲባል (በዚህ አገባቡ) የወንድን ከወገብ በታች የሚሸፍን የሆነ ልብስ ሁሉ የሚመለከት ነው። ይህም ሶስት ሁኔታዎች አሉት: የመጀመሪያው: ተወዳጅ የሆነ ነው። ይህም እስከ ባቱ ግማሽ ድረስ አሳጥሮ ማድረግ ነው። ሁለተኛው: ሳይጠላ የሚፈቀድ ነው። ይህም ከባቱ ግማሽ በታች እስከ ቁርጭምጭሚቱ ድረስ ባለው አሳጥሮ ማድረጉ ነው። ቁርጭምጭሚት ማለት በባትና እግር መካከል የሚለየው እብጥ ያሉት አጥንቶች ናቸው። ሶስተኛው: ክልክል የሆነው ነው። ይህም ከቁርጭምጭሚት በታች መሆኑ ነው። ይህም እሳት እንዳያገኘው ይፈራለታል። ከቁርጭምጭሚቱ በታች ያስረዘመው በኩራት፣ በመመፃደቅና በጥመት ከሆነ ደግሞ አላህ ወደርሱ አይመለከትም።
03
Benefits
ይህ ባህሪና ዛቻ በወንዶች ላይ ብቻ የተገደበ ነው። ሴቶች እዚህ ውስጥ አይካተቱም። ምክንያቱም እነርሱ ሰውነታቸውን ባጠቃላይ እንዲሸፍኑ የታዘዙ ስለሆኑ ነው።
የወንድን ከወገብ በታች የሚሸፍን የሆነ ልብስ ሁሉ "ኢዛር" ተብሎ ይጠራል። እንደሱሪና ሌሎች ልብሶች ይመስል። እነዚህ ሁሉ ልብሶች እዚህ ሐዲሥ ውስጥ የተጠቀሰው ሸሪዓዊ ህግጋት ውስጥ ይገባሉ።
የወንድን ከወገብ በታች የሚሸፍን የሆነ ልብስ ሁሉ "ኢዛር" ተብሎ ይጠራል። እንደሱሪና ሌሎች ልብሶች ይመስል። እነዚህ ሁሉ ልብሶች እዚህ ሐዲሥ ውስጥ የተጠቀሰው ሸሪዓዊ ህግጋት ውስጥ ይገባሉ።
Attribution
[አቡዳውድ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

