ለኩራት ልብሱን የጎተተን ሰው አላህ አይመለከተውም።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከኢብኑ ዑመር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ለኩራት ልብሱን የጎተተን ሰው አላህ አይመለከተውም።"
Explanation
Benefits
ልብስ በማርዘም ዙሪያ የመጣው ክልከላ ወንዶችን ብቻ ነው የሚመለከተው። ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ዑለማዎች ባጠቃላይ ለሴት ልጅ ማርዘም እንደሚፈቀድ ተስማምተዋል። ሴቶች የቀሚሳቸውን ጫፍ አንድ ስንዝር እንዲለቁ ከነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ፍቃድ መገኘቱ ተረጋግጧል።"
ኢብኑ ባዝ እንዲህ ብለዋል: "ልብስን ማርዘም የሐዲሦች ጥቅል ሀሳብ ስለሚጠቁም ክልክልና ሐራም ነው። ቅጣቶቹ ግን ይበላለጣሉ። የግድ እኩል መሆንም አይጠበቅባቸውም። ኩራትን አስቦ ያስረዘመ ሰው የሚቀጣው ቅጣት ሳያስብ እንዳስረዘመው አይደለም።"
ኢብኑ ባዝ እንዲህ ብለዋል: "ሴት ልጅ መላ አካሏ ሀፍረተ ገላ ነው። ስለዚህም ልብሷን አንድ ስንዝር ወደታች ብትለቅ ከልካይ የላትም። አንድ ስንዝር ራሱ ካልበቃት ከቁርጭምጭሚቷ ጀምራ አንድ ክንድ ወደ ታች ትለቃለች።"
ቃዲ እንዲህ ብለዋል: «ዑለማዎች እንዲህ ብለዋል: "በጥቅሉ በልብስ ዙሪያ ከአስፈላጊውና ከተለመደው ርዝማኔም ይሁን ስፋት የጨመረ ሁሉ ይጠላል።" ይበልጡን አላህ ያውቃል።»
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ከጀለቢያና ከሽርጥ ጫፍ (ከጉልበት ስር) ወደ ታች ከሚወርደው ተወዳጁ መጠን የባት ግማሽ ድረስ ነው። ከባት ግማሽ እስከ ቁርጭምጭሚት መሃል ድረስ ቢያደርገውም ችግር የለውም። ከቁርጭምጭሚት ዝቅ ካለ ግን እርሱ እሳት ውስጥ ነው። ተወዳጁ የባት ግማሽ ድረስ ሲሆን ሳይጠላ የሚፈቀደው ደግሞ ከባት ግማሽ በታች እስከ ቁርጭምጭሚት ድረስ ነው። ከቁርጭምጭሚት ዝቅ ያለው ደግሞ የተከለከለው ነው።"
ኢብኑ ዑሠይሚን (አላህ ወደርሱ አይመለከትም።) በሚለው ዙሪያ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ማለት የእዝነትና የርህራሄ እይታ አያየውም ማለት ነው እንጂ በጥቅሉ አያየውም ማለት አይደለም። ምክንያቱም አላህ በርሱ ላይ አንዳችም አይደበቅበትም፤ አንዳችም ነገር ከእይታው አይሰወርበትምም። ነገር ግን ከሐዲሡ የተፈለገው የእዝነትና የርህራሄ እይታ ነው።"
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

