افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم. افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم. افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم. افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم. افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم. افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم. افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم. افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم.
#66370[ሶሒሕ ነው።]
HadeethEnc · 1.23.0

ከናንተ ምርጡ እኔ ያለሁበት (ዘመን) ትውልድ ነው። ከዚያም ከነርሱ በኋላ ቀጥለው የሚመጡት፤ ከዚያም ከነርሱ ቀጥለው የሚመጡት ናቸው።

Available translations

Choose an available translation of this Hadeeth

01

Hadeeth text

ከዒምራን ቢን ሑሰይን (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ከናንተ ምርጡ እኔ ያለሁበት (ዘመን) ትውልድ ነው። ከዚያም ከነርሱ በኋላ ቀጥለው የሚመጡት፤ ከዚያም ከነርሱ ቀጥለው የሚመጡት ናቸው።" ዒምራንም እንዲህ አለ: "ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከሳቸው ትውልድ በኋላ ሁለት ትውልዶችን ይጥቀሱ ወይም ሶስት አላውቅም።" ከዚያም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ: "የሚከዱ የማይታመኑ፤ ምስክርነት ሳይጠየቁ የሚመሰክሩ፤ ስለትን ተስለው ስለታቸውን የማይሞሉ፤ በነርሱ ላይ ደንዳና ሰውነት የሚስተዋልባቸው ሰዎች ከናንተ በኋላ ይመጣሉ።"»
02

Explanation

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በአንድ ዘመን ከሚኖሩ ማህበረሰቦችና ትውልዶች መካከል ምርጡ ማህበረሰብና ትውልድ የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እና ሶሐቦች የነበሩበት ማህበረሰብና ትውልድ መሆኑን ተናገሩ። ቀጥሎ ደግሞ ከዛ ቀጥለው የመጡ የአላህን መልክተኛ ሳያገኙ ሶሓቦችን ያገኙ አማኞች መሆናቸውን ተናገሩ። ቀጥሎ ደግሞ ከዛ ቀጥለው የመጡ አትባዑ ታቢዒኖች ናቸው። ይህን ሐዲሥ የተናገረው ሶሓባ አራተኛው ትውልድ በመጠቀሱ ዙሪያ አመንትቷል። ቀጥለው ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "ከነዚህ በኋላ ሰው የማይተማመንባቸው ከዳተኞች የሆኑ፤ ለምስክርነት ሳይጠየቁ በፊት ምስክርነትን የሚሰጡ፤ ስለት ተስለው ስለታቸውን የማይሞሉ፤ ውፍረት በግልፅ እስኪስተዋልባቸው ድረስ መብላትና መጠጣት የሚያበዙ ሰዎች ይመጣሉ።" አሉ።
03

Benefits

ዱንያ ካለፈባት ዘመን ባጠቃላይ ምርጡ ዘመንና ትውልድ ነቢዩና (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሶሓቦች ያሳለፉት ዘመን ነው። በሶሒሕ ቡኻሪ እንደመጣው ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "እኔ የኖርኩበት ትውልድ እስኪመጣ ድረስ ከነበሩት ሁሉ መልካም የሆነ ከአደም ልጆች ሁሉ ከምርጥም ምርጥ ትውልድ ላይ ተላኩኝ።"
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ ሶሐቦች ከታቢዒዮች የበለጡ መሆናቸውን፤ ታቢዒዮች ደግሞ ከአትባዑ ታቢዒን የበለጡ መሆናቸውን ያስይዛል። ነገር ግን ይህ በላጭነት እንደ ጥቅል ነው ወይስ በተናጠልም ጭምር ነው? የሚለው ጥያቄ ጥናት የሚፈልግ ጉዳይ ነው። አብዛኛዎቹ ዑለማ ግን ሁለተኛውን አቋም መርጠዋል።"
የሶስቱን የመጀመርያ ትውልዶች መንገድ አጥብቆ በመከተል ላይ መጠቆሙን ያስረዳናል። ዘመኑ ለነቢያዊው ዘመን የቀረበ በሆነ ቁጥር በደረጃና በእውቀት የበለጠ ለመሆን እንዲሁም የነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) መመሪያ ለመከተል የተገባ ነውና።
ስለት ማለት: አንድ ለአቅመ አዳም የደረሰና አይምሮው ጤነኛ የሆነ ሰው ግዴታነትን በሚጠቁም ማንኛውም ንግግር አላህ ግዴታ ያላደረገበትን አንድን አምልኮ ራሱ ላይ ግዴታ ማድረጉ ነው።
ከዳተኝነት፣ ስለትን አለመሙላትና ቀልብን በዱንያ ማንጠልጠል መወገዙን እንረዳለን።
ባለመብቱ ምስክር ሊሆነው እንደሚችል እያወቀም ምስክርነት ሳይጠይቀው መመስከር መወገዙን እንረዳለን። ባለመብቱ እርሱ ምስክር እንደሆነ ካላወቀው ግን "ምርጡን ምስክር አልነግራችሁምን? ሳይጠየቅ በፊት ለመመስከር የሚመጣ ምስክር ነው።" የሚለው የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ንግግር ውስጥ የሚካተት ነው።

Attribution

[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

Categories

Share

Share hadeeth

Sharing options · 0 Total shares

Share

← Back to encyclopedia
Shopping Basket

Loading...