እኔ ከናንተ መካከል ፍፁም ወዳጅ ከመያዝ ወደ አላህ እጥራራለሁ። ምክንያቱም የላቀው አሏህ ኢብራሂምን ፍፁም ወዳጅ
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከጁንዱብ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፡ "ነብዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከመሞታቸው አምስት (ሌሊቶች) በፊት እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፡- ' እኔ ከናንተ መካከል ፍፁም ወዳጅ ከመያዝ ወደ አላህ እጥራራለሁ። ምክንያቱም የላቀው አሏህ ኢብራሂምን ፍፁም ወዳጅ አድርጎ እንደያዘው ሁሉ እኔንም ፍፁም ወዳጅ አድርጎ ይዞኛልና። ከኡመቴ መካከል ፍፁም ወዳጅ አድርጌ የምይዝ ብሆን ኖሮ አቡበከርን ነበር ፍፁም ወዳጅ አድርጌ የምይዘው። አዋጅ! እነዚያ ከናንተ በፊት የነበሩት የነብያቶቻቸውንና የፃድቃኖቻቸውን መቃብር መስገጃ ስፍራ አድርገው ይይዙ ነበር። አዋጅ! መቃብርን መስገጃ ስፍራ አድርጋችሁ አትያዙ! እኔ እየከለከልኳችሁ ነው።'"
Explanation
Benefits
በመቃብር ላይ መስገጃ መገንባት ያለፉት ህዝቦች ከሚፈፅሟቸው ውግዝ ተግባራት መካከል ነው።
መቃብርን የአምልኮ ስፍራ አድርጎ መያዝ፣ መቃብር አጠገብም ሆነ ወደርሷ ዞሮ መስገድ፣ ወይም በላያቸው ላይ መስገጃ ወይም ጉልላት መስራት ወደ ሽርክ ሊያደርስ ስለሚችል ተከልክሏል።
በፃድቃን ላይ ድንበር ማለፍ ወደ ሽርክ ሊያደርስ ስለሚችል መጠንቀቅ ይገባል።
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከመሞታቸው አምስት ቀናት ቀደም ብለው ማስጠንቀቃቸው ያስጠነቀቁት ጉዳይ ያለውን አደገኝነት ያሳያል።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

