HadeethEnc · 1.23.0
ዝምድናን ቆራጭ ጀነት አይገባም።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከጁበይር ቢን ሙጥዒም -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እርሱ ነቢዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰማቸው: "ዝምድናን ቆራጭ ጀነት አይገባም።"
02
Explanation
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለቅርብ ዘመዶቹ ያለበትን ግዴታ ከመወጣት ይልቅ ዝምድናውን የቆረጠ ሰው ወይም ያወካቸውና ያስከፋቸው ጀነት ላለመግባት የተገባ ነው ብለው ተናገሩ።
03
Benefits
ዝምድናን መቁረጥ ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል አንዱ ነው።
ዝምድናን መቀጠል በተለምዶ በሚታወቀው መልኩ ነው የሚሆነው። ቦታ፣ ዘመንና ሰዎቹ እንደመለያየታቸው ይለያያል።
ዝምድናን መቀጠል በመዘየር፣ ሶደቃ በመስጠት፣ ለነርሱ በጎ በመዋል፣ ሲታመሙ በመጠየቅ፣ በመልካም በማዘዝ፣ ከመጥፎ በመከልከልና በሌሎችም መልኩ ይፈፀማል።
ዝምድናው የሚቆረጠው ሰው እጅግ ቅርብ ዘመድ በሆነ ቁጥር ወንጀሉም እጅግ የከፋ ይሆናል።

Attribution
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares