HadeethEnc · 1.23.0
በአላህ ገንዘብ ያለአግባብ የሚገለገሉ ሰዎች ለነርሱ የትንሳኤ ቀን እሳት ተዘጋጅቶላቸዋል።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከኸውለህ አልአንሷሪይ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ አለች: ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: "በአላህ ገንዘብ ያለአግባብ የሚገለገሉ ሰዎች ለነርሱ የትንሳኤ ቀን እሳት ተዘጋጅቶላቸዋል።"
02
Explanation
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሙስሊሞችን ገንዘብ ያለአግባብ ስለሚጠቀሙና ያለአግባብ ስለሚበዘብዙ ሰዎች ተናገሩ። ይህም ገንዘብን ባልተፈቀደ መልኩ ማጠራቀምና ማግኘትን እንዲሁም ትክክለኛ ባልሆነ ቦታ ፈሰስ ማድረግን የሚጠቀልል ሀሳብ ነው። የየቲሞችን ገንዘብ መብላት፣ ወቅፍ የተደረገን ገንዘብ መብላት፣ አደራዎችን መካድ፣ የማህበረሰቡን ገንዘብ ያለአግባብ መውሰድ ሁሉ እዚህ ውስጥ ይካተታል።
ቀጥለውም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የትንሳኤ ቀን የነዚህ ሰዎች ምንዳ እሳት መሆኑን ተናገሩ።
ቀጥለውም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የትንሳኤ ቀን የነዚህ ሰዎች ምንዳ እሳት መሆኑን ተናገሩ።
03
Benefits
በሰዎች እጅ ያሉ ገንዘቦች አላህ በደነገገላቸው መንገድ እንዲያወጡትና ያለአግባብ ከመገልገል ይርቁ ዘንድ ሰዎችን ምትክ ያደረገበት የአሏህ ገንዘቡ ነው። ይህም መሪዎችንም ሆነ ሌሎችንም አጠቃላይ ሰዎችን የሚጠቀልል ነው።
ሸሪዓ በማህበረሰቡ ገንዘብ ዙሪያ ጥብቅ መሆኑን እንረዳለን። ከገንዘብ በጥቂቱም ቢሆን የተሾመ ሰው የትንሳኤ ቀን ስለገንዘቡ አሰባሰብም ሆነ ስለአወጣጡ ይተሳሰባል።
የራሱንም ገንዘብ ሆነ የሌላውን ገንዘብ ሸሪዓዊ ባልሆነ መልኩ የሚገለገልም በዚህ ዛቻ ይካተታል።
ሸሪዓ በማህበረሰቡ ገንዘብ ዙሪያ ጥብቅ መሆኑን እንረዳለን። ከገንዘብ በጥቂቱም ቢሆን የተሾመ ሰው የትንሳኤ ቀን ስለገንዘቡ አሰባሰብም ሆነ ስለአወጣጡ ይተሳሰባል።
የራሱንም ገንዘብ ሆነ የሌላውን ገንዘብ ሸሪዓዊ ባልሆነ መልኩ የሚገለገልም በዚህ ዛቻ ይካተታል።
Attribution
[ቡኻሪ ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares