አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን በሰላምታ አትጀምሯቸው። ከመካከላቸው አንዱን መንገድ ላይ ባገኛችሁ ጊዜም ወደ ጠባቡ መንገድ አጣብቡት።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን በሰላምታ አትጀምሯቸው። ከመካከላቸው አንዱን መንገድ ላይ ባገኛችሁ ጊዜም ወደ ጠባቡ መንገድ አጣብቡት።"
Explanation
Benefits
እነርሱ ሰላምታውን ከጀመሩ "ወዐለይኩም" በማለት ለነርሱ ሰላምታን መመለስ ይፈቀዳል።
አንድ ሙስሊም ከሃዲያንን ሆን ብሎ ማወክ አይፈቀድለትም። ለምሳሌ ወደ ጠባቡ መንገድ እንዲሄድ አስገዳጅ ነገሮች ሳይኖሩ ሆን ብሎ ማጣበብን ይመስል። ነገር ግን መንገዱ ጠባብ ወይም የተጨናነቀ ከሆነ በዛ መንገድ ቀድሞ የማለፍ መብት ያለው ሙስሊሙ ነው። ከሀዲው ዘወር ይበልለት።
ያለምንም ግፍ ወይም በንግግር ሳናስቀይም የሙስሊሞች የበላይነትና የሌሎች ደግሞ መተናነስ ግልፅ መሆን እንዳለበት እንረዳለን።
ከሃዲያንን በአላህ ላይ ባላቸው ክህደት ምክንያት ማጣበብ የመስለማቸው ምክንያት ሊሆንም ይችላል። ይህ ምክንያቱን እንዲያውቁ ካደረጋቸው ሰልመው ከእሳት እንዲድኑ ምክንያት ሊሆናቸው ይችላል።
አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አንድ ሙስሊም ለከሃዲ ቀድሞ እንዴት ነህ? ደህና አደርክ? ደህና አመሸህ?ና የመሳሰሉትን ማለቱ ችግር የለም። ክልከላው የሚተረጎመው በሰላምታ (አሰላሙ ዓለይኩም ማለት) ላይ ነው።
ጢቢይ እንዲህ ብለዋል: «የቢድዓ ሰውም ቀደም ተብሎ በሰላምታ አይጀመርም የሚለው ተመራጭ አቋም ነው። የማያውቀውን ሰው ሰላምታ ጀምሮ በቃልኪዳን የሚኖር ከሃዲ ወይም የቢድዓ ሰው መሆኑ ግልፅ ከሆነለት እርሱን ለማሳነስ በሚል "ሰላምታዬን መልሻለሁ ተሳስቼ ነው።" ይለዋል።»
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

