HadeethEnc · 1.23.0
ከዱንያ ቸልተኛ ሁን አላህ ይወድሃል። ሰዎች ዘንድ ካለው ቸልተኛ ሁን ሰዎች ይወዱሃል።" አሉት።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአቡል ዓባስ ሰህል ቢን ሰዕድ አስሳዒዲይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - በመምጣት እንዲህ አለ፡ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ብሰራው አላህም የሚወደኝ ሰዎችም የሚወዱኝ የሆነን ስራ ጠቁሙኝ!" እርሳቸውም: "ከዱንያ ቸልተኛ ሁን አላህ ይወድሃል። ሰዎች ዘንድ ካለው ቸልተኛ ሁን ሰዎች ይወዱሃል።" አሉት።»
02
Explanation
አንድ ሰውዬ ሲሰራው አላህም የሚወደው ሰዎችም የሚወዱት የሆነን ስራ ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲጠቁሙት ጠየቀ። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንደዱንያ ትርፍ የሆኑ እንደ አኺራም የማይጠቅሙ የሆኑ ነገሮችን በተውክና ዲንህ ላይ ጉዳት የሚያስከትሉብህን ነገሮች የተውክ ጊዜ አላህ ይወድሃል። ሰዎች እጅ ያለን የዱንያ ጥቅም ችላ ያልክ ጊዜ ደሞ ሰዎች ይወዱሃል። ምክንያቱም ሰዎች በተፈጥሯቸው ንብረታቸውን ይወዷታልና በንብረታቸው የተጋፋቸውን ይጠሉታል። ንብረታቸውን የተወላቸውን ደግሞ ይወዱታል በማለት መለሱለት።
03
Benefits
በዱንያ ውስጥ ዛሂድ የመሆን ትሩፋትን እንረዳለን። ዙህድ ማለት: ለመጪው አለም የማይጠቅምን ነገር መተው ማለት ነው።
የዙህድ ደረጃው ከወረዕ የበለጠ ነው። ወረዕ ማለት የሚጎዳን ነገር መተው ማለት ሲሆን ዙህድ ግን ለመጪው አለም የማይጠቅምን ነገር መተው ማለት ነው።
ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: "ዱንያ ሰዎች ዘንድ ተወዳጅ ናት። በሷ ጉዳይ የሚጋፋቸውን ሰው በተጋፋቸው መጠን እነርሱ ዘንድ የተጠላ ይሆናል። እነርሱንና የሚወዱትን የተወላቸው ሰው ደሞ በዛ ልክ በቀልባቸው ውስጥ ተወዳጅ ይሆናል።

Attribution
[رواه ابن ماجه وغيره بأسانيد حسنة]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares