በምን ጉዳይ ላይ ነው ቃልኪዳን የምንጋባዎት?› አልናቸው። እርሳቸውም ‹አላህን በርሱ አንዳችም ሳታጋሩ በመገዛት፣ በአምስቱ ሶላቶች ላይ፣ በታዛዥነት፣ (ዝግ ባለ ድምፅ የተወሰኑ ቃላቶችን ተናገሩ።) ሰዎችን አንዳችም ነገር ባለመጠየቅ።› አሉን።'
ከአቡ ሙስሊም አልኸውላኒ እንደተላለፈው እንዲህ አሉ "ተወዳጁና ታማኙ ሰው ይህንን ሐዲሥ ነገረኝ። እርሱ እኔ ዘንድ ተወዳጅነትም ታማኝነትም አለው። ይሀውም ዐውፍ ቢን ማሊክ አልአሽጀዒይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ አሉ: 'የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ ዘጠኝ ወይም ስምንት ወይም ሰባት ሆነን ሳለ እንዲህ አሉን ‹ለአላህ…

