ዉዱእን አዳርሰህ አድርግ። በጣቶችህ መካከል ፈልፍል። ፆመኛ እስካልሆንክ ድረስም አፍንጫህ ውስጥ ውሃ ስትከት በደንብ አስገባ።" አሉኝ።
ለቂጥ ቢን ሰቢራህ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንዲህ አሉ: «ወደ አላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ከተላኩ የበኒ አልሙንተፊቅ ወይም በበኒ አልሙንተፊቅ ልዑክ ውስጥ ነበርኩ። የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ ስንደርስ በቤታቸው አላገኘናቸውም ነበር። የአማኞች እናትን ዓኢሻን አገኘን። በስጋና ዱቄት የሚሰራ (ኸዚራ) የሚባል ምግብ እንዲሰ…

