በመጨረሻው ዘመን እድሜያቸው ለጋ፣ አስተሳሰባቸው የሞኝ የሆኑ ሰዎች ይመጣሉ። ከፍጡራን ንግግር የተሻለን ንግግርም ይናገራሉ። ቀስት (ኢላማውን) በስቶ እንደሚወጣው እነርሱም ከእስልምና ይወጣሉ።
ከዐሊይ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ከአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የነገርኳችሁ ጊዜ በርሳቸው ላይ ውሸትን ከምቀጥፍ ከሰማይ ብፈጠፈጥ እመርጣለሁ። በኔና በናንተ መካከል ባለ ጉዳይ ከነገርኳችሁ ግን ፍልሚያ ሽወዳ ነው። የአላህን መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈ…

