ሰዎች ግፈኛን ተመልክተው እጁን ካልያዙት አላህ ከርሱ በሆነ ቅጣት ሊያጠቃልላቸው ይቀርባል።
ከአቡበከር አስሲዲቅ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «እናንተ ሰዎች ሆይ! {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁን (ከእሳት) ያዙ! (ጠብቁ)። በተመራችሁ ጊዜ የተሳሳተ ሰው አይጎዳችሁም።} የሚለውን አንቀፅ ታነቡታላችሁ። እኔ የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "ሰዎች ግፈኛን ተመልክተው እጁን ካልያዙት አላህ…

