በአላህ እምላለሁ! ከናንተ መካከል አንዱ ያለአግባብ አንዳችን አይወስድም የትንሳኤ ቀን ተሸክሞት አላህን ቢገናኝ እንጂ
ከአቡ ሑመይድ አስሳዒዲይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - አንድ ኢብኑ ሉትቢየህ ተብሎ የሚጠራን ሰውዬ የበኒ ሱለይምን ጎሳ ዘካ እንዲሰበስብ ሾሙት፤ ሰብስቦ ሲመጣም ተሳሰቡት። እርሱም ሲያስረክብ እንዲህ አለ: "ይህ የናንተ ገንዘብ ነው። ይህ ደሞ የተሰጠኝ ስጦታ ነው።" የአላህም መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእ…

