በአላህ እምላለሁ! ከናንተ መካከል አንዱ ያለአግባብ አንዳችን አይወስድም የትንሳኤ ቀን ተሸክሞት አላህን ቢገናኝ እንጂ
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአቡ ሑመይድ አስሳዒዲይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - አንድ ኢብኑ ሉትቢየህ ተብሎ የሚጠራን ሰውዬ የበኒ ሱለይምን ጎሳ ዘካ እንዲሰበስብ ሾሙት፤ ሰብስቦ ሲመጣም ተሳሰቡት። እርሱም ሲያስረክብ እንዲህ አለ: "ይህ የናንተ ገንዘብ ነው። ይህ ደሞ የተሰጠኝ ስጦታ ነው።" የአላህም መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ አሉ: "እውነት ላንተ የተሰጠ ስጦታ ከሆነ ስጦታው ቤትህ እስኪመጣ ድረስ እናት አባትህ ቤት አትቀመጥም ነበር?" ቀጥለውም ኹጥባ አደረጉልን: አላህን ካመሰገኑና ካወደሱ በኋላም እንዲህ አሉ: "ከዚህ በመቀጠል እኔ አላህ በሰጠኝ ሹመት መሰረት ከናንተ መካከል አንድን ሰው ከሾምኩት በኃላ እኔ ዘንድ በመምጣት ይህ የናንተ ገንዘብ ነው። ይህ ደግሞ የተሰጠኝ ስጦታ ነው ይላል እንዴ?! ስጦታው ቤቱ እስኪመጣለት ድረስ እናት አባቱ ቤት አይቀመጥም ነበር? በአላህ እምላለሁ! ከናንተ መካከል አንዱ ያለአግባብ አንዳችን አይወስድም የትንሳኤ ቀን ተሸክሞት አላህን ቢገናኝ እንጂ ከናንተ መካከል አላህ ፊት የምትጮህ ግመል ወይም የምታጋሳ ከብት ወይም የምትጮህ በግ ተሸክሞ የሚቀርብን ሰው አውቃለሁ።" ቀጥለው "አላህ ሆይ መልዕክቴን አድርሻለሁን?" እያሉ የብብታቸው ንጣት እስኪታይ ድረስ እጃቸውን ከፍ አደረጉ። ይህንን ሁሉ አይኔም አይቷል ጆሮዬም ሰምቷል።»
Explanation
Benefits
የሰዎችን ገንዘብ በግፍ የሚወስድ ሰው እንደተዛተበት እንረዳለን።
የትንሳኤ ቀን የበደላትን ይዞ የሚመጣ ቢሆን እንጂ መምጣቱ የሚቀር አንድም በዳይ የለም።
በማንኛውም የመንግስት ስራ ላይ ተመድቦ የሚሰራ ቅጥረኛ ካሉበት ግዴታዎች መካከል የተመደበበትን ስራ መፈፀም ነው። ለርሱም ከስራው ጋር ተያይዘው የሚመጡን ስጦታዎች መቀበል አይፈቀድለትም። ከተቀበለም ወደ ግምጃ ቤት ይክተት። ወደ መጥፎና እምነትን ወደማጓደል ስለሚያደርስ ለራሱ መጠቀም አይፈቀድለትም።
ኢብኑ በጧል እንዲህ ብለዋል: "ሐዲሡ እንደሚጠቁመው ለሰራተኛ የሚሰጥ ስጦታ ወይ ውለታውን ለማመስገኛ ይሆናል ወይም የርሱን ውዴታ ለማግኘት ይሆናል ወይም ካለበት ግዴታ እንዲያነሳለት በመከጀል ይሆናል። ነቢዩም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለርሱ የሚሰጠውን ስጦታ እንደማንኛውም ሙስሊም መሆን እንዳለበትና ለርሱ ከሌላው ሙስሊም ተለይቶ ስጦታ የሚያሰጠው ምንም ደረጃ ስለሌለው እርሱን ከሌላው መለየት እንደማይፈቀድ ተናገሩ።"
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ከዚህ ሐዲሥ እንደምንረዳው: ለቅጥር ሰራተኞች የሚሰጥ ስጦታ ክልክልና ስርቆት እንደሆነ ነው። ይህም የተሰጠውን ሃላፊነትና አደራ ስለከዳ ነው። ለዚህም ሐዲሡ ውስጥ ቅጣቱ የትንሳኤ ቀን የተሰጠውን ስጦታ በመሸከም እንደሆነ ተጠቀሰ። ምርኮ የሚሰርቅ ሰውም ተመሳሳይ ቅጣት እንደሚቀጣ በሌላ ሐዲሥ ተጠቅሷል። ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እዚሁ ሐዲሥ ውስጥ ለርሱ ስጦታ መስጠት የተከለከለበትን ምክንያት ገልፀዋል። እርሱም ሃላፊነት ላይ የተቀመጠ ስለሆነ ነው። ቅጥር ስራው ላይ ላልሆነ ሰው ስጦታ መስጠት ግን የሚከለከል ሳይሆን ተወዳጅ ተግባር ነው።"
ኢብኑል ሙኒር እንዲህ ብለዋል: «"አባት እናቱ ቤት አይቀመጥም ነበርን?" ከሚለው ነቢያዊ ንግግር ከዚህ በፊት ስጦታ ይሰጠው ከነበረ ሰው ከሹመት በኋላም ስጦታውን መቀበል እንደሚፈቀድ እንወስዳለን። ኢብኑ ሐጀርም እንዲህ ብለዋል: "ይህም የሚፈቀደው በተለምዶ ከተለመደው የስጦታ መጠን ካልጨመረ እንደሆነ ግልፅ ነው።"»
የነቢያዊ ምክር አሰጣጥ ጠቅለል አድርጎ መምከር ነው እንጂ ስሙን እየጠሩ መምከር አይደለም።
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ከዚህ ሐዲሥ አደራ የተጣለበት የሆነን ሰው መተሳሰብ የተደነገገ እንደሆነ እንረዳለን።"
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ከዚህ ሐዲስ የተሳሳተን ሰው ማጥላላትም የሚፈቀድበት አጋጣሚ እንዳለ እንረዳለን።"
በዱዓ ወቅት ሁለት እጆችን ከፍ ማድረግ እንደሚወደድ እንረዳለን።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

