አንድ ሰው ሌላን ሰው በአመፀኝነትም ሆነ በከሃዲነት አያነውረውም ባለቤቱ እንደዚያ ካልሆነ ወደርሱ ብትመለስ እንጂ።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአቡዘር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እርሱ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምተዋል: "አንድ ሰው ሌላን ሰው በአመፀኝነትም ሆነ በከሃዲነት አያነውረውም ባለቤቱ እንደዚያ ካልሆነ ወደርሱ ብትመለስ እንጂ።"
Explanation
Benefits
በሰዎች ላይ በሚሰጡ ፍርዶች ማረጋገጥ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
ኢብኑ ደቂቅ አልዒድ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ ከሙስሊሞች መካከል አንድን ሰው እርሱ ከሃዲ ሳይሆን ከሃዲ ለሚል ሰው ትልቅ ዛቻ ነው። ይህም ትልቅ ጣጣ ነው።"
ኢብኑ ሐጀር አልዓስቀላኒይ እንዲህ ብለዋል: «ነገር ግን በዚህ ንግግሩ እውነቱን ከሆነ አመፀኛ ወይም ከሃዲ አይሆንም ሲባል "አንተ አመፀኛ" በሚለው ንግግሩ ምንም ወንጀለኛ ሊሆን አይችልም የሚለውን አያሲዝም። ይልቁንም ይህ ሁኔታ በዝርዝር መታየት ይገባዋል። "አንተ አመፀኛ" ሲለው የፈለገበት እርሱን መምከር ወይም የርሱን ሁኔታ ለሌሎች በመግለፅ ሌሎችን መምከር ከሆነ ይፈቀዳል። እርሱን ማነወር፣ ወንጀል መስራቱ እንዲታወቅ ለማድረግና ለመጉዳት ብቻ አስቦ ከሆነ ግን አይፈቀድም። ምክንያቱም እርሱ የታዘዘው እንዲሸሽግለት፣ በመልካም መልኩ እንዲያስተምረውና እንዲመክረው ነው። ይህንን በልስላሴ ማስተማር እስከቻለ ድረስ በሀይል መፈፀሙ አይፈቀድለትም። በሀይል መምከሩ አብዛኛው ሰው እልህ ውስጥ ገብቶ እንደሚያደርገው እንዲጠምና በዛ ወንጀል ላይ እንዲዘወትር ምክንያት ይሆናልና። በተለይ አዛዡ ከታዛዡ በደረጃ ዝቅ ያለ የሆነ ጊዜ ይህ ይከሰታል።»
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

