HadeethEnc · 1.23.0
መሳሪያውን በኛ ላይ ያነሳ ከኛ አይደለም።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአቡ ሙሳ አልአሽዐሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "መሳሪያውን በኛ ላይ ያነሳ ከኛ አይደለም።"
02
Explanation
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለማስፈራራት ወይም ንብረታቸውን ለመቀማት በሙስሊሞች ላይ መሳሪያ ከማንሳት አስጠነቀቁ። ያለ አግባብ ይህንን የፈፀመም ትልቅ ሀጢአትንና ወንጀልን መፈፀሙን ለዚህ ከባድ ዛቻም መጋረጡን አሳሰቡ።
03
Benefits
ሙስሊም ከሙስሊም ወንድሙ ጋር መጋደሉ ብርቱ ማስጠንቀቂያ የመጣበት ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን።
በምድር ላይ ከሚሰሩ ትላልቅ ወንጀሎችና ብክለቶች መካከል መሳሪያን በሙስሊሞች ላይ ማንሳትና በመግደል ማበላሸት አንዱ ነው።
የተጠቀሰው ዛቻ ወሰን አላፊዎችን፣ አጥፊዎችንና ሌሎችም የመሳሰሉትን በሀቅ (በሸሪዓ በተፈቀደ ምክንያት) መጋደልን አያካትትም።
ለቀልድ እንኳ ቢሆን ሙስሊሞችን በመሳሪያ ወይም በሌላ ነገር ማስፈራራት መከልከሉን እንረዳለን።

Attribution
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares