የከለከልኳችሁን ነገር ራቁ፤ ካዘዝኳችሁም ነገር የቻላችሁትን ያህል ፈፅሙ!
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ ዐብዱራሕማን ቢን ሶኽር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: "የከለከልኳችሁን ነገር ራቁ፤ ካዘዝኳችሁም ነገር የቻላችሁትን ያህል ፈፅሙ! ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች ያጠፋቸው ጥያቄ ማብዛታቸውና ነቢያቶቻቸውን መቃረናቸው ነው።"»
Explanation
Benefits
ክልከላን ለመዳፈር ምንም የተግራራ መንገድ የለም። ትእዛዝን ለመፈፀም ግን በመቻል ገደብ ተገደበ። ይህም የሆነው መተው የሚጠይቀው አቅም ስለሌለና መስራት ግን የታዘዙትን ድርጊት ለማስገኘት የሚጠይቀው አቅም ስላለ ነው።
ጥያቄን ማብዛት መከልከሉን እንረዳለን። ዑለማዎች መጠየቅን ለሁለት ከፍለውታል: አንደኛው: የሚያስፈልገውን ሃይማኖታዊ ጉዳይ በመማር መልኩ መጠየቅ ነው። በዚህ አላማ መጠየቅ ታዟል። የሶሐቦችም ጥያቄ በዚህ መልኩ ነበር። ሁለተኛው: ጥያቄን ለመፍጠር በመጨነቅና በግትርነት መልኩ መጠየቅ ሲሆን ይህኛው ግን የተከለከለው የመጠየቅ አይነት ነው።
ይህ ኡማ ከዚህ በፊት የነበሩት ህዝቦች ነቢያቸውን እንደተቃረኑት ነቢያቸውን ከመቃረን መከልከላቸውን እንረዳለን።
ክልከላን መራቅ ትንሹንም ብዙውንም ያካተተ ነው። ምክንያቱም ሐራምን መራቅ የሚገኘው ትንሹንም ብዙውንም በመራቅ ብቻ ነውና። ለምሳሌ መልክተኛው ከአራጣ ከለከሉን። ይህ ክልከላ ትንሹንም ብዙውንም አራጣ ያካትታል።
ወደ ሐራም የሚያደርሱ ምክንያቶችን መተው እንደሚገባ እንረዳለን። ምክንያቱም መራቅ የሚለው ትርጓሜ ከነመዳረሻዎቹ መራቅን የሚያጠቃልል ነውና።
አንድ ሰው የመልክተኛውን -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ትእዛዝ በሰማ ጊዜ ግዴታ ነው ወይስ ተወዳጅ ነው ብሎ መጠየቅ አይገባውም። ይልቁንም ለመተግበር ነው መቻኮል ያለበት። ይህም "የቻላቹትን ያህል ፈፅሙ!" ከሚለው የምነወስደው ትምህርት ነው።
ጥያቄ ማብዛት በተለይ የሩቅ ጉዳዮችን፣ የትንሳኤ ቀንን የሚመለከት አይነቱ መልሱ ሊደረስበት የማይችል ጉዳይ ላይ አብዝቶ መጠየቅ የጥፋት ምክንያት ነው። ይህን በመሰሉ ጉዳዮች ጥያቄ አታብዛ ትጠፋለህም፤ ወሰን የሚያልፍም ትሆናለህ።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

