ፀሀይ ከወጣችባቸው ቀናቶች ሁሉ በላጩ ቀን የጁመዓ ቀን ነው።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው : ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ፀሀይ ከወጣችባቸው ቀናቶች ሁሉ በላጩ ቀን የጁመዓ ቀን ነው። በዚህ ቀን ኣደም ተፈጠረ፣ በዚሁ ቀን ጀነት ገባ፣ በዚሁ ቀን ከርሷ ወጣ፣ ሰአቲቱም በጁመዓ ቀን ካልሆነ በቀር አትከሰትም።"
Explanation
Benefits
በጁሙዓ ቀን መልካም ስራዎችን በማብዛት ላይ፣ የአላህን እዝነት ለማግኘት በመዘጋጀትና መአቱን በመከላከል ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
ሐዲሡ ውስጥ የተጠቀሱት እነዚህ የጁመዓ ቀን መለዮዎች እንጂ የጁመዓን ቀን ደረጃ ለመጥቀስ ተብለው የተወሱ አይደሉም። የአደም ከጀነት መውጣትና የትንሳኤ ቀን መቆም ደረጃ ተደርገው አይቆጠሩም ያሉ ሲኖሩ፤ በሌላ በኩል ደግሞ እዚህ ሐዲሥ ውስጥ የተጠቀሱት ሁሉም ደረጃዎች ናቸው። የአደም ከጀነት መውጣት ከመልክተኞች፣ ከነቢያቶችና ከደጋጎች የሆኑ ዘሮችን ለማግኘት ሰበብ ሲሆን የትንሳኤ መቆም ደግሞ የደጋጎች ምንዳ ለመፍጠኑና አላህ ለነርሱ ያዘጋጀላቸውን መከበሪያ ለማግኘት ሰበብ ስለሆነ ነው ያሉም አሉ።
በዚህ ዘገባ ያልተጠቀሱ በሌላ ዘገባ ግን የተጠቀሱ የጁመዓ ቀን ሌሎች መለዮዎችም አሉ። ከነሱም መካከል: በጁመዓ እለት አላህ የአደምን ተውበት ተቀበለ፣ በጁመዓ እለት ሞተ፣ በዚህች ቀን አንድ አማኝ ባሪያ እየሰገደ አላህን አንዳች ነገር እየጠየቀ ይህቺን ሰዓት አያገኝም አላህ የጠየቀውን የሚሰጠው ቢሆን እንጂ የተባለላት አንዲት ሰዓት አለች።
በዓመት ከሚገኙ ቀናቶች በላጩ ቀን የዐረፋ ቀን ነው። የእርድ ቀን ነው ያሉም አሉ። ከሳምንት ቀናቶች ሁሉ በላጩ ቀን የጁሙዓ ቀን ነው። በላጩ ምሽት ደግሞ የለይለተል ቀደር ምሽት ነው።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

