HadeethEnc · 1.23.0
አንዳችሁ ወንድሙ ላይ መሳሪያን አይደቅን። አይታወቅም ምናልባት ሸይጧን መሳሪያውን ከእጁ ላይ ይወሰውሰውና በእሳት ጉድጓድ ውስጥ ሊጥለው ይችላልና።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦ "አንዳችሁ ወንድሙ ላይ መሳሪያን አይደቅን። አይታወቅም ምናልባት ሸይጧን መሳሪያውን ከእጁ ላይ ይወሰውሰውና በእሳት ጉድጓድ ውስጥ ሊጥለው ይችላልና።"
02
Explanation
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አንድ ሙስሊም ወደ ሙስሊም ወንድሙ ማንኛውንም የመሳሪያ አይነት ከመደቀን አስጠነቀቁ። ምናልባት ሳይታወቀው እጁ ላይ ባለው መሳሪያው ሸይጧን ወስውሶት ወንድሙን እንዲገድል ወይም እንዲጓዳ ሊያደርገው ይችላልና። በዚህም የእሳት ጉድጓድ ውስጥ ወደ ለመጣል የሚያደርሰው ወንጀል ላይ ይወድቃል።
03
Benefits
የሙስሊም ደም ያለው ክብር መገለፁ።
ሙስሊምን ማክበር ግዴታ መሆኑንና በንግግርም ይሁን በተግባር እርሱ ላይ መጥፎን ነገር ማድረስ መከልከሉን እንረዳለን። ከዚህም መካከል ስለት ወይም መሳሪያ ለቀልድ እንኳ ቢሆን እርሱ ላይ መደቀን ነው። ሸይጧን እጁን በመጎትጎት ወንድሙን መምታትን ሊያስውብለት ይችላል። ወይም መሳሪያው ከእጁ ላይ በማንቀሳቀስ ሳይፈልገው ወንድሙ ላይ ታርፍና ወንድሙን ትጎዳለች።
ወደ ክልክል ነገር የሚያደርስን ነገር መንገዱን በመዝጋት መዳረሻው መከልከሉን እንረዳለን።
ለማህበረሰቡ ደህንነትና በሰዎች መካከል ያለውን መስተጋብር ለመጠበቅ ጥረት መደረጉንና በመደቀንና በመዛት እንኳ ቢሆን ማህበረሰብን ማስደንገጥና ማስፈራራት እንደማይገባ እንረዳለን።

Attribution
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares