HadeethEnc · 1.23.0
በአላህ ጌትነት፣ በእስልምና ሃይማኖትነት፣ በሙሐመድ መልክተኝነት ወድጃለሁ ያለ ሰው ጀነት ለርሱ ፀንታለታለች።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "በአላህ ጌትነት፣ በእስልምና ሃይማኖትነት፣ በሙሐመድ መልክተኝነት ወድጃለሁ ያለ ሰው ጀነት ለርሱ ፀንታለታለች።"
02
Explanation
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) (ረዲቱ ቢላሂ ረብበን) በአላህ አምላክነት፣ ተንከባካቢነት፣ ንጉስነት፣ አለቃነት፣ አስተካካይነት ወድጃለሁ፤ (ወቢልኢስላሚ) በእስልምና በሁሉም ትእዛዛዊና ክልከላዊ ህግጋቶቹ (ዲነን) መንገድነት፣ ሃይማኖትነትና እምነትነት ወድጃለሁ፤ (ወቢሙሐመደን ረሱላ) በሙሐመድ ነቢይነት፣ እርሳቸው በተላኩበትና ወደኛ ባደረሱት ነገር ሁሉ ወድጃለሁ ያለ ሰው ጀነት ለርሱ እንደፀናችለት ተናገሩ።
03
Benefits
ይህን ዱዓ በማለት ላይ መነሳሳቱንና ይህንን ዱዓ ማለትን ተከትሎ የሚገኘው ምንዳ መገለፁን እንረዳለን።
በአላህ ጌትነት መውደድ ሲባል ሰውዬው ከአላህ ሱብሓነሁ ውጪ ያለን አለመገዛቱንም ያካትታል።
በሙሐመድ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ነቢይነትና መልክተኝነት መውደድም ነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) መታዘዝና ለሱናቸው ተገዢ መሆንን ያካትታል።
በእስልምና ሃይማኖትነት መውደድ ሲባል አላህ ለባሮቹ የመረጠውን መውደድ ማለት ነው።
በሌላ ዘገባ እንደመጣው አዛን በሚባልበት ጊዜ ሁለቱን የምስክርነት ቃላት ካለ በኋላ ይህን ዱዓ ማለት ይወደዳል።
በሌላ ሐዲሥ እንደመጣው ደሞ ይህን ዱዓ ንጋትና ምሽት ላይ ማለትም ይወደዳል።

Attribution
[አቡዳውድ ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares