“የአንድ ሰው እስልምናው ያማረ ለመሆኑ ምልክቱ የማይመለከተውን ነገር መተዉ ነው።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል፦ “የአንድ ሰው እስልምናው ያማረ ለመሆኑ ምልክቱ የማይመለከተውን ነገር መተዉ ነው።"
Explanation
Benefits
ዛዛታ፣ ትርፍ ንግግሮችንና ከንቱ ተግባራትን መተው የሰውዬውን እስልምና መሙላት የሚጠቁም ነው።
ሁሉም ሰው ለዲኑና ለዱንያው በሚጠቅመው ጉዳይ ላይ እንዲጠመድ መነሳሳቱን እንረዳለን። የሰውዬው እስልምና የሚዋበው የማይጠቅመውን ሲተው ከሆነ የእስልምናው ውበት የሚጨምረው ደግሞ በሚጠቅመው ላይ በመጠመዱ ነው ማለት ነው።
ኢብኑል ቀይዪም አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል: «ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ በማለት በአንድ ንግግር ጥንቁቅነትን በሙሉ ጠቅልለው ገለፁት: "የአንድ ሰው እስልምናው ያማረ ለመሆኑ ምልክቱ የማይመለከተውን ነገር መተዉ ነው።" ይህም የማይጠቅምን ንግግር፣ እይታ፣ መስማት፣ መጨበጥ፣ መጓዝ፣ ማሰብና ሌሎችንም ውጫዊና ውስጣዊን እንቅስቃሴን መተው ያቀፈ ንግግር ነው። ይህቺ ንግግር ጥንቁቅነት ለመግለፅ ፍቱን የሆነች ቃል ናት።»
ኢብኑ ረጀብ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ ከአደብ መሰረቶች መካከል አንዱ መሰረት ነው።"
የሰው ልጅ የሚጠቅመውንና የማይጠቅመውን የሚያውቀው በመማር ስለሆነ በዚህ ሐዲሥ እውቀትን መፈለግ ተበረታቷል።
በመልካም ማዘዝ፣ ከመጥፎ መከልከልና ሰውን መምከር ትእዛዝ የተላለፈበት ጉዳይ ስለሆነ ለሰው ከሚጠቅሙ ነገሮች መካከል የሚመደቡ ናቸው።
የሐዲሡ ጥቅል ሃሳብ ውስጥ ከሚካተቱ ነገሮች መካከል: አላህ ዐዘ ወጀል ከከለከላቸው፣ ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - የጠሉት ነገር የማይጠቅሙ ስለሆኑ መራቅ እንደሚያስፈልግ ነው። ልክ እንደዚሁ የማያስፈልጉ የመጪው አለም ጉዳዮችን እንደሩቅ እውቀት እውነታ፣ ስለ አላህ የመፍጠር ሂደትና ትእዛዛት ጉዳይ በዝርዝር ማጥናት፣ ስለ አላህ ቅድመ ውሳኔ ጉዳዮች መጠየቅና መመራመር፣ ያልተከሰቱን ወይም ከነአካቴው ሊከሰቱ ስለማይችሉ ነገሮች ቢከሰቱስ ብሎ መጠመድ የሐዲሡ ጥቅል ውስጥ የሚካተቱ የማይጠቅሙ ጉዳዮች ናቸው።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

