HadeethEnc · 1.23.0
ሶላትን የረሳ ሰው ባስታወሰው ጊዜ ይስገድ። ከዚህ በቀር ማካካሻ የለውም።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "ሶላትን የረሳ ሰው ባስታወሰው ጊዜ ይስገድ። ከዚህ በቀር ማካካሻ የለውም። {ሶላትንም (በርሷ) እኔን ለማስታወስ ስገድ።} [ጣሀ:14]
02
Explanation
የትኛውንም የግዴታ ሶላት ወቅቱ እስኪወጣ ድረስ መስገድን የረሳ ሰው ባስታወሰ ወቅት ቀዷእ ለማድረግ መፍጠን እንደሚገባውና አንድ ሙስሊም በወቅቱ መስገድን በመተዉ ለፈፀመው ወንጀልም ባስታወሰ ወቅት መስገዱ እንጂ ሌላ ምንም ማበሻና ማስማሪያ እንደሌለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገለፁ። አላህ በተከበረው መጽሐፉ እንዲህ ብሏል {ሶላትንም (በርሷ) እኔን ለማስታወስ ስገድ።} [ጣሀ:14] ማለትም የተረሳን ሶላት ባስታወስካት ወቅት ቀጥ አድርገህ ስገድ ማለትም ነው።
03
Benefits
የሶላት አንገብጋቢነት እና በወቅቱ ከመፈፀምና ቀዷእ ከማድረግ መሳነፍ እንደማይገባ መገለፁን እንረዳለን።
ያለሸሪዓዊ ምክንያት ሶላትን ከወቅቱ ሆን ብሎ ማዘግየት እንደማይፈቀድ እንረዳለን።
የረሳ ሰው ባስታወሰ ወቅት፣ የተኛ ሰው ደግሞ በነቃ ወቅት ሶላትን ቀዷእ ማድረግ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
በተከለከለ ወቅት እንኳን ቢሆን ሶላትን በፍጥነት ቀዷእ ማድረግ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
ያለሸሪዓዊ ምክንያት ሶላትን ከወቅቱ ሆን ብሎ ማዘግየት እንደማይፈቀድ እንረዳለን።
የረሳ ሰው ባስታወሰ ወቅት፣ የተኛ ሰው ደግሞ በነቃ ወቅት ሶላትን ቀዷእ ማድረግ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
በተከለከለ ወቅት እንኳን ቢሆን ሶላትን በፍጥነት ቀዷእ ማድረግ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
Attribution
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

