የዐስርን ሶላት የተወ ሰው በርግጥም ስራው ተበላሸ።'
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከቡረይዳህ ቢን ሑሰይብ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ "የዐስርን ሰላት ወቅቱ እንደገባ ቶሎ ስገዱ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋልና: ' የዐስርን ሶላት የተወ ሰው በርግጥም ስራው ተበላሸ።'"
Explanation
Benefits
የዐስርን ሶላት በተወ ሰው ላይ ብርቱ ዛቻ መምጣቱንና ዐስርን ከወቅቱ ማሳለፍ ሌሎችን ሶላቶች ከወቅቱ ከማሳለፍ የበለጠ እጅግ ከባድ መሆኑን እንረዳለን። የዐስር ሶላት {በሶላቶች (በተለይ) በመካከለኛይቱም ሶላት ላይ ተጠባበቁ፡፡} [አልበቀራህ: 238] በሚለው የአላህ ንግግር ላይ ባለው ትእዛዝ ልዩ ሆና የተወሳች ምርጧ ሶላት ናትና።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

