'አላህ በዳይን ያዘገየዋል። የያዘው ጊዜ ግን አይለቀውም!
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአቡ ሙሳ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: 'አላህ በዳይን ያዘገየዋል። የያዘው ጊዜ ግን አይለቀውም!'" አቡ ሙሳ እንዲህ አለ: "ቀጥለውም {የጌታህም ቅጣት የከተሞችን ሰዎች እነሱ በዳዮች ሲሆኑ በቀጣቸው ጊዜ እንደዚህ ነው። ቅጣቱ በእርግጥ አሳማሚ ብርቱ ነው።} [ሁድ: 102] የሚለውን አነበቡ።"
Explanation
ቀጥለውም ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም {የጌታህም ቅጣት የከተሞችን ሰዎች እነሱ በዳዮች ሲሆኑ በቀጣቸው ጊዜ እንደዚህ ነው። ቅጣቱ በእርግጥ አሳማሚ ብርቱ ነው።} [ሁድ: 102] የሚለውን አነበቡ።
Benefits
አላህ በዳዮችን ማዘግየቱና እነሱን በመቅጣት አለመቻኮሉ እነሱን ማዘናጊያና ካልቶበቱ ቅጣታቸውን ማነባበርያ ነው።
ግፍ የአላህን ቅጣት ህዝቦች ላይ የሚያመጣ አንዱ ምክንያት ነው።
አላህ አንድን መንደር ሲያጠፋ በውስጧ ደጋጎችም ሊኖሩ ይችላሉ። እነዚህ ደጋጎች የትንሳኤ ቀን በሞቱበት መልካምነት ላይ ሆነው ነው የሚቀሰቀሱት። ምድራዊ ቅጣቱ እነሱንም ማካተቱ በመጪው አለም አይጎዳቸውም።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

