HadeethEnc · 1.23.0
(ጎረቤቴን) ያስወርሰዋል ብዬ እስከማስብ ድረስ ጂብሪል በጎረቤት (ሐቅ ዙሪያ) እኔን ከማዘዝ አልተወገደም።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከኢብኑ ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "(ጎረቤቴን) ያስወርሰዋል ብዬ እስከማስብ ድረስ ጂብሪል በጎረቤት (ሐቅ ዙሪያ) እኔን ከማዘዝ አልተወገደም።"
02
Explanation
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጂብሪል ለጎረቤታቸው ትኩረት እንዲቸሩ፣ ሐቁን እንዲጠብቁ፣ እንዳያውኩት፣ ለርሱ በጎ እንዲውሉ፣ በሚያደርስባቸው ጉዳት እንዲታገሱ ከማዘዝና ከመደጋገም እንዳልተወገደ ተናገሩ። ይህም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከጎረቤት ሀቅ ክብደትና ጂብሪል ይህን ትእዛዝ ከመደጋገሙ የተነሳ ከሞቱ በኋላ ትተውት የሚያልፉትን ገንዘባቸውን ለጎረቤታቸው እንዲሰጡ የሚያዝ ወሕይ ሊወርድ ይሆን ብለው እስኪያስቡ ደረሱ። ጎረቤት ሲባልም ሙስሊምም ሆነ ካፊር፣ ዘመድም ሆነ ባዳ ማንኛውም ለቤት ቅርብ የሆነ ማለት ነው።
03
Benefits
የጎረቤት ሐቅ ክብደትንና ይህንን መጠባበቅ ግዴታ እንደሆነ እንረዳለን።
የጎረቤት ሐቅ በአደራ መልክ መጠንከሩ ጎረቤትን ማክበርን፣ መውደድን፣ ለርሱ በጎ መዋልን፣ ከርሱ ጉዳትን መከላከልን፣ ሲታመም መጠየቅን፣ በደስታ ወቅት ማስደሰትን፣ በመከራ ወቅት ማፅናናትን ያስፈርዳል።
የጎረቤት ደጃፍ በቀረበ ልክ ሐቁም የጠነከረ ይሆናል።
ሸሪዓ ለጎረቤት በጎ መዋልና ከነሱ ላይ ጉዳትን መከላከልን የመሰለ ለማህበረሰቡ ጥቅም ያላቸው ድንጋጌዎችን ይዞ በመምጣቱ ረገድ የተሟላ መሆኑን እንረዳለን።

Attribution
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares