ሁሉም ህዝቦቼ ጀነት ይገባሉ እምቢ ያለ ሲቀር
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና-እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡ "ሁሉም ህዝቦቼ ጀነት ይገባሉ እምቢ ያለ ሲቀር" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ማን እምቢ ይላል?" አሉ። እሳቸውም "እኔን የታዘዘኝ ጀነት ገባ ፤ እኔን ያመፀኝ ደግሞ በርግጥም እምቢ ብሏል።" በማለት መለሱ።"
Explanation
ሰሐቦችም አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ማን ራሱን ከጀነት ያቅባል?" አሉ።
እሳቸውም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም : "መልክተኛውን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የተከተለና የታዘዘ ጀነት ገባ። ያመፀና ለሸሪዐ ታዛዥ ያልሆነ ሰው ግን በርግጥም በመጥፎ ስራዎቹ ጀነት ከመግባት ራሱን አቅቧል።" በማለት መለሱላቸው።
Benefits
ነቢዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መታዘዝ ጀነት መግባትን ስታስፈርድ እሳቸውን ማመፅ ደግሞ እሳት መግባትን የምታስፈርድ መሆኗን እንረዳለን።
ከዚህ ኡማህ አላህና መልክተኛውን ያመፁ ሲቀሩ ነቢዩን ታዛዥ የሆኑ ሁሉ ጀነት ይገባሉና ለነርሱ ብስራት ነው።
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በኡመታቸው ላይ ያላቸውን እዝነትና እንዲመሩ ያላቸውን ጥልቅ ጉጉት እንረዳለን።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

