አንዳችሁ በየቀኑ አንድ ሺህ ምንዳ መሸመት ይሳነዋልን?
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከሰዕድ ቢን አቢ ወቃስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ ነበርን። እንዲህም አሉን: "አንዳችሁ በየቀኑ አንድ ሺህ ምንዳ መሸመት ይሳነዋልን?" ከተቀመጡት ሰዎች መካከል አንድ ጠያቂ "እንዴት ነው አንዳችን አንድ ሺህ ምንዳ የሚሸመተው?" በማለት ጠየቃቸው። እርሳቸውም: "መቶ ጊዜ ተስቢሕ ካለ ለርሱ አንድ ሺህ ምንዳ ይፃፍለታል ወይም ከርሱ ላይ አንድ ሺህ ወንጀል ይሰረዝለታል።" በማለት መለሱ።»
Explanation
Benefits
ተስቢሕና ዚክር የማድረግን ደረጃ እንረዳለን። ይህም ሰው በማይከብደው ትንሽ ስራ አማካኝነት ይህንን ያህል ትልቅ ምንዳ ያስገኛልና።
ሶሓቦች መልካም ስራዎችን ሳያዘገዩ ለመስራት ይቻኮሉ እንደነበረ እንረዳለን።
መልካም ስራዎች በአስር ይባዛሉ። ይህንንም በማስመልከት አላህ እንዲህ ብሏል: (በመልካም ስራ የመጣ ሰው ለርሱ አስር ብጤዎቿ አሉት።) [አልአንዓም: 160] ይህም ትንሹ የብዜት ደረጃ ነው። እንጂማ እስከ ሰባት መቶ እጥፍ ድረስ እንደሚባዛም ተዘግቧል።
በዚህ ሐዲሥ አንዳንድ ዘገባዎች (ወይም ከርሱ አንድ ሺህ ወንጀል ይሰረዝለታል።) ከሚለው ነቢያዊ ንግግር (ወይም) የሚለው ቃል ሳይጠቀስ (و) (ሁለቱንም እንደሚያገኝ በሚጠቁም መስተፃምር) መጥቷል። ቃሪይ እንዲህ ብለዋል: "አንዳንዴ (و) (ወይም) የሚለውን ትርጉም ለመጠቆም ትመጣለች። በሁለቱ ዘገባዎች መካከል መጋጨት የለውም። ትርጉሙም: ይህቺን ዚክር ያለ ሰው በርሱ ላይ ወንጀል ከሌለበት አንድ ሺህ ምንዳ ይፃፍለታል። በተወሰነው ይሰረዝለታል በተወሰነው ይፃፍለታል ማለት ነው። ወይም ደግሞ (ወይም) በአረብኛው (او) የምትለዋ ቃል የተፈለገባት (و) ወይም (بل) ማለት ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ ይህንን ዚክር ያለ ሰው ሁለቱንም ያገኛል ማለት ነው። የአላህ ችሮታ ከዚህም በላይ ነውና።" ተጠናቀቀ። ማለትም አንድ ሺህ ምንዳም ያገኛል። አንድ ሺህ ወንጀሉም ይሰረዝለታል እንደማለት ነው።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

