HadeethEnc · 1.23.0
'ሲዋክ አፍን የሚያጠራ (የሚያፀዳ)፤ የአሏህንም ውዴታ የሚያስገኝ ነው።'
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከዓኢሻህ ረዲየሏሁ ዐንሃ እንደተላለፈው እንዲህ አለች፡ "የአሏህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፡ 'ሲዋክ አፍን የሚያጠራ (የሚያፀዳ)፤ የአሏህንም ውዴታ የሚያስገኝ ነው።'"
02
Explanation
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አራክ በተባለው ወይም በአምሳያው በሆነ መፋቂያ ጥርስን መፋቅ አፍን ከቆሻሻ እና ከመጥፎ ጠረን እንደሚያፀዳ ነገሩን። ይህንኑ ማድረግም ለአሏህ ታዛዥነትና ለትእዛዙ ምላሽ መስጠት ከመሆኑ ባሻገር አሏህ የሚወደውን ንፅህናንም የሚያስተርፍ ስለሆነ ድርጊቱ የአሏህን ውዴታ ማግኛ ሰበብ መሆኑን ነገሩን።
03
Benefits
ጥርስን መፋቅ ያለውን ትሩፋትና ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዑመታቸው ድርጊቱን ያበዛ ዘንድ ማነሳሳታቸውን እንረዳለን።
ቢፍቁበት የተሻለው "አራክ" የተባለውን የዛፍ ግንድ (መፋቂያ) ከመሆኑም ጋር በምትኩ የጥርስ ብሩሽ ከሳሙናው ጋር መጠቀምም ይቻላል።
ቢፍቁበት የተሻለው "አራክ" የተባለውን የዛፍ ግንድ (መፋቂያ) ከመሆኑም ጋር በምትኩ የጥርስ ብሩሽ ከሳሙናው ጋር መጠቀምም ይቻላል።
Attribution
[ነሳኢና አሕመድ ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

