HadeethEnc · 1.23.0
አምስቱ ከተፈጥሯዊ (ኢስላማዊ ሱናዎች) ናቸው፦ መገረዝ፣ የብልትን ፀጉር መላጨት፣ ቀድሞ ቀመስን (ከአፍንጫ ስር ያለን ፂም) ማሳጠር፣ ጥፍሮችን መቁረጥና የብብትን ፀጉር መንጨት።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ "አምስቱ ከተፈጥሯዊ (ኢስላማዊ ሱናዎች) ናቸው፦ መገረዝ፣ የብልትን ፀጉር መላጨት፣ ቀድሞ ቀመስን (ከአፍንጫ ስር ያለን ፂም) ማሳጠር፣ ጥፍሮችን መቁረጥና የብብትን ፀጉር መንጨት።
02
Explanation
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከመልክተኞች ሱናዎችና ከኢስላማዊ መገለጫዎች መካከል አምስቱን አብራሩ፦
የመጀመሪያው፦ መገረዝ ነው። እሱም ከወንድ ልጅ ብልት ከክርክሩ ከፍ ብሎ ያለውን ጭማሪ ቆዳና ከሴት ልጅ ብልት ደግሞ ከወንድ ብልት መግቢያ ስፍራ ከፍ ብሎ ያለውን ቆዳ ከጫፉ ቀንሶ መቁረጥ ነው።
ሁለተኛው: የብልትን ፀጉር መቁረጥ ነው። ይህም ከብልት ዙሪያ ያለውን ፀጉር መላጨት ነው።
ሶስተኛው: ቀድሞ ቀመስን ማሳጠር: እሱም በወንድ ልጅ የላይኛው ከንፈር ላይ የበቀለን ፂም ከንፈሩ በግልፅ እስኪታይ መቁረጥ ነው።
አራተኛው: ጥፍሮችን መቁረጥ ነው።
አምስተኛው: የብብትን ፀጉር መንጨት ነው።

03
Benefits
አላህ የሚወዳቸውና ያዘዘባቸው የሆኑ የመልክተኞቹ ሱናዎች ወደ ምሉእነት፣ ንፅህናና ቁንጅና የሚጣሩ መሆናቸውን እንረዳለን።
እነዚህን ነገሮች ተጠባብቆ መፈፀም የተደነገገ መሆኑንና ከነዚህ ጉዳዮች አለመዘናጋት እንደሚገባ እንረዳለን።
እነዚህን ጉዳዮች በአግባቡ መፈፀም ዲናዊና አለማዊ ጥቅሞች አሉት። ከነሱም ውስጥ፦ አካልን ማስዋብ፣ ሰውነትን ማፅዳት፣ ለንፅህና ጥንቁቅ መሆን፣ ከሀዲያንን መቃረንና የአላህን ትእዛዝ መፈፀም ይገኝበታል።
በሌላ ሐዲሥ ውስጥ ከነዚህ አምስት ተፈጥሯዊ ሱናዎች ውጪ ያሉ ተጨማሪ ሱናዎች፤ ለምሳሌ: ፂምን መልቀቅ (ማፋፋት)፣ ሲዋክና ሌሎችም ተጠቅሰዋል።

Attribution
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares