ውሻ ከአንዳችሁ እቃ የጠጣ ጊዜ (እቃውን) ሰባት ጊዜ ይጠበው።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ውሻ ከአንዳችሁ እቃ የጠጣ ጊዜ (እቃውን) ሰባት ጊዜ ይጠበው።"» ሙስሊም ባስተላለፉት ደግሞ "አንዱን በአፈር በመቀላቀል ይጠበው።" የሚል ተዘግቧል።
Explanation
Benefits
ውሻ እቃ ውስጥ ምላሱን በመንከር መጠጣቱ እቃውንም ውስጡ ያለውን ውሃም ይነጅሰዋል።
በአፈር ማፅዳትና በውሃም ሰባት ጊዜ መደጋገም የውሻ ሽንት፣ ሰገራና ሌሎችም ውሻ ያቆሸሻቸው ነገሮች የሚፀዱበት አፀዳድ ሳይሆን በአፉ የነካ ጊዜ ብቻ የሚፈፀም የአፀዳድ አይነት ነው።
እቃ በአፈር የሚፀዳበት የአፀዳድ አፈፃፀም: እቃ ውስጥ ውሃ ያደርግና አፈር ይጨምርበታል። ቀጥሎ በዚህ ከአፈር ጋር በተቀላቀለ ውሃ የተነጀሰውን እቃ ያጥባል።
የሐዲሡ ግልፅ መልዕክት ሸሪዓ ቤታችን እንድናደርጋቸው የፈቀዳቸውን ውሻዎችንም ሳይቀር የአደን፣ የጥበቃ፣ ለአዝርእትና ከብቶች ጥበቃ የምናሳድጋቸውን ውሻዎች ይመስል ሁሉንም ውሻዎች ያጠቃልላል።
ሳሙናና እንዶድ የአፈርን ቦታ አይተኩም። ይህም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለይተው አፈር ብለው በግልፅ ስላስቀመጡ ነው።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

