እኔ የበኑ ሰዕድ ቢን በክር ወንድም ዲማም ቢን ሠዕለባህ ነኝ።" አላቸው።
አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ መስጂድ ውስጥ ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ጋር ተቀምጠን ሳለ አንድ ግመል ላይ ያለ ሰውዬ ገባ። መስጂድ ውስጥ ግመሉን ካንበረከከ በኋላ አሰራት። ከዚያም ለነሱ እንዲህ አላቸው፦ "ማንኛችሁ ነው ሙሐመድ?" ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በመካከላቸው ተደግፈው ነበር። "ይህ የተደገፈው ቀይ ሰውዬ ነው።" አልነው…

