እነሆ የሚዋሹና ግፈኛ የሆኑ መሪዎች ይመጣሉ። ውሸታቸውን አምኖ የተቀበለና በበደላቸው ላይ ያገዛቸው እርሱም ከኔ አይደለም። እኔም ከርሱ አይደለሁም።
ከሑዘይፋህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "እነሆ የሚዋሹና ግፈኛ የሆኑ መሪዎች ይመጣሉ። ውሸታቸውን አምኖ የተቀበለና በበደላቸው ላይ ያገዛቸው እርሱም ከኔ አይደለም። እኔም ከርሱ አይደለሁም። ወደኔ ምንጭም (ወደ ሐውድ) አይመጣም። የነርሱን ውሸት አምኖ ያልተቀበለና በበደላቸውም ላ…

