የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንድ ሰው ገንዘቤን ለመውሰድ ፈልጎ ቢመጣ እስኪ ንገሩኝ ምን ላድርግ?
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «አንድ ሰውዬ ወደ አላህ መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ በመምጣት እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንድ ሰው ገንዘቤን ለመውሰድ ፈልጎ ቢመጣ እስኪ ንገሩኝ ምን ላድርግ?" እርሳቸውም "ገንዘብህን እንዳትሰጠው" አሉት። እርሱም "ከተጋደለኝስ?" አላቸው። እርሳቸውም "አንተም ተጋደለው።" አሉት። እርሱ…

